Addis Zemen (Aug 29, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከፍለ ከተማ አስተዳደር የወረዳ 01 ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት የሚሆን በ1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ለአገልግሎት የሚውል የፅህፈት መሳሪያ፤ ቋሚ እቃ፤ ደንብ ልብስ፤ የፅዳት እቃ፤ የጥገና እቃ የጥገና ስራ፤ የጭነት አገልግሎት፤ ህትመት፤ የህክምና ማሽን እቃ አክሰሰሪ፤ የመድሀኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት እና የህከምና ዕቃ የልብስ ስፌት በ 2019/01 አንደኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የእቃው አይነት |
የሎት አይነት |
የጨረታ ማሰከበሪያ |
|
1 |
የፅህፈት መሳሪያ |
ሎት 1 |
15000 |
|
2 |
ቋሚ እቃ |
ሎት 2 |
15202 |
|
3 |
ደንብ ልብስ |
ሎት 3 |
14500 |
|
4 |
የፅዳት እቃ |
ሎት 4 |
6602 |
|
5 |
የጥገና እቃ |
ሎት 5 |
7000 |
|
6 |
የጥገና ስራ |
ሎት 6 |
10000 |
|
7 |
የመኪና ጭነት አገልግሎት |
ሎት 7 |
4000 |
|
8 |
ህትመት |
ሎት 8 |
8000 |
|
9 |
የህክምና ማሽን አክሰሰሪ |
ሎት 9 |
2500 |
|
10 |
የመድሀኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት የህክምና እቃ |
ሎት 10 |
10000 |
|
11 |
የልብሥ ስፌት ስራ |
ሎት 11 |
2500 |
|
ጅምላ ንግድ የሆነ ሲፒኦ ደምሮ በአንድ ማምጣት ይችላል። |
|||
በዚህ መሠረት:-
1. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና አግባብ ባለው የመንግስት ተቋም የተሰጠ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ፣ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉት ኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልበት ዕቃን ወይም አገልግሎትን ለማቅረብ በሚሆንበት ጊዜ፣ ለኤክሳይዝ ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምዝገባ ሰርተፍኬት
2. ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠ የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት በጤና ጣቢያው ረዳት ፋይናንስ ቢሮ 4ተኛ ፎቅ ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
4. እንዳስፈላጊነቱ የብቃት ማረጋገጫ ሰነዶች፣ ከአምራች ወይም ከአከፋፋዮች የሚሰጥ ውክልና ወይም የእሽሙር ማህበር መመስረቻ ሰነድ እንዲሁም ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶች ተካተው መቅረብ አለበት።
5. ተጫራቾች ሳምፕል ለተጠየቁበት እቃዎች ሳምፕል የማቅረብ ግዴታ አለባቸው እንዲሁም የጨረታ ሰነዳቸውን በማሸግ ጤና ጣቢያው ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
6. ጨረታው በአስረኛው ቀን ከቀኑ በ11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በቀጣይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን በጤና ጣቢያው ፋይናንስ የስራ ሂደት 4ተኛ ፎቅ ይከፈታል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ አሟልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ዋጋ የለውም።
8. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. በማምረት ስራ ላይ ለተሰማሩ ጥቃቅን እና አነሰተኛ ተቋማት አካል ጉዳተኛች፤ የነጋዴ ሴቶች ማህበራት፤ እንዲሁ በቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶቻቸው ከተደራጁበት ወረዳ ወቅታዊ እና ባደራጀችሁ አካል እሴት መጨመራቸሁን የሚያሳውቅ ደብዳቤ በዋና ስራ አስፈፃሚ በአድራሻቸውን ማቅረብ ይኖርባችሁዋል።
አድራሻ፡– ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ጤና ጣቢያ ከለቡ ፍርድ ቤት በስተጀርባ በተለምዶ ቫርኔሮ አደባባይ ፊት ለፊት
ስልክ 09-12-09-87-70 / 09-37-90-98-72
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 01 ጤና ጣቢያ