በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት የቢሮ አላቂ እቃዎች ስቴሽነሪ እና የሞተር ሳይክል መለዋወጫ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት የቢሮ አላቂ እቃዎች ስቴሽነሪ እና የሞተር ሳይክል መለዋወጫ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Aug 31, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የምስራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በስሩ ላሉ መስሪያ ቤቶች የሚውል

  • የቢሮ አላቂ እቃዎች ስቴሽነሪ እና 
  • የሞተር ሳይክል መለዋወጫ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ፥ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ስለ እቃዎቹ የሚገልጽ የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 200(ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት በምስ/አዘ/በር/ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በመምጣት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡

በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች

 የዘመኑ ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ ፤የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tin Number) ማቅረብ የሚችሉ

የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል

የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

ተጫራቾች ለጨረታው

  • ሎት ı ለቢሮ አላቂ እቃዎች ጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ 35,000 ብር ማቅረብ የሚችሉ
  • ሎት 2 ለሞተር ሳይክል መለዋወጫ ዕቃዎች ጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ 40,000 ብር ማቅረብ የሚችሉ

5. ተጫራቾች በጨረታው ያሸነፉትን እቃ ምስ/አዘ/በ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ የትራንስፖርት የማስጫኛና የማውረጃ ጨምሮ በጨረታው ሰነድ ላይ በመሙላት ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኢንቭሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ21 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. አንዱ ባቀረበው ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

8. ጨረታው በ21ኛው ቀን የቢሮ አላቂ እቃዎች (ስቴሽነሪ) በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በቀኑ 8፡30 ሰዓት እንዲሁም የሞተር ሳይክል መለዋወጫ በ9፡00 ሰዓት ታሽጎ በቀኑ 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል፡፡

9. በተጫራቾች ተሞልተው የሚቀርቡ ፋይናንሻል ዋጋዎች በግልጽና በጥራት የሚታዩና ስርዝ ወይም ድልዝ ያልሆኑ መሆን አለባቸው፡፡

10. ተጫራቾች በሚፈልጉት ዕቃ ላይ መወዳደር ይችላሉ ሆኖም ለአንድ እቃ ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይቻልም፡፡

11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. ወረዳው ከአዲስ አበባ ርቀቱ 221 ኪሎ ሜትር ሲሆን 176 ኪሎ ሜትር አስፓልት እና 45 ኪሎ ሜትር ፒስታ መንገድ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 21 33 86 96/09 33 62 02 20

ቂልጦ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መ/በስልጤ ዞን የምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *