Addis Zemen (Sep 01, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም ለመስሪያ ቤቱ ስራ አገልግሎት የሚውሉ፡-
- ሎት.1 የደንብ ልብስ
- ሎት2. የትምህርት አላቂ እቃዎች
- ሎት 3 .የፅዳት እቃዎች
- ሎት4, ቋሚ እቃ
- ሎት 5 የስፖርት እቃዎች
- ሎት6፡- ልዩ ልዩ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ በዘርፉ የተሰማራቹ ህጋዊ ነጋዴዎችን በጨረታ አወዳድረን በጥራት እና በዋጋ በማወዳደር አሸናፊ ከሆኑት ድርጅቶች ለመግዛት የምንፈልግ መሆኑን እያሳወቅን፤
- ተጫራቾች የ2019 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN)የተሰጠው፤
- ወቅታዊ የ2018 ዓ.ም የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በጨረታው መሣተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- በኢፌድሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ሊስት (Supplier List) ውስጥ የተመዘገቡ፤
- በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን የሚገልጽ የጨረታ ተሳትፎ ከገቢዎችና ጉምሩክ ጽ/ቤት ቀኑ ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 / ሶስት መቶ ብር) በመከፈል የሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል ከጠዋቱ 2፡30-11፡30 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ ህጋዊ የድርጅት ማህተምና ፊርማ ማደረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የእቃዎች ዝርዝር ላይ የእያንዳንዱን ዋጋ በመሙላት በ2 በታሸገ ኤንቨሎፕ ሰነዱን አሽገው ዋናውን እና ኮፒውን ለያይተው ጨረታው እስከሚያበቃበት 1ኛው ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከዋለ ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በዕለቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ (ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም)፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪ ሰነድ ለይ የሚያቀርቡት የእቃ አይነት ዋጋ ስርዝ ዱልዝ የሌለበት ስልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽና ህጋዊ ማህተም ያረፈበት ሊሆን ይገባል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ዋጋ ላይ የዋጋ ለውጥም ሆነ ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለጸለት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ቅሬታ ተጠብቆ ከ8-15 ቀን ውስጥ በተወዳደሩበት ዋጋ እና በቴክኒክ አሸናፊነታቸው ከተገለጸለቻው በኋላ ቀርቦ የውል ማስከበርያ 10%/አስር ፐርሰንት CPO/ ለግዢ ፈጻሚ አካል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ያሸነፈ ተጫራች ለአሸነፋቸው ዕቃዎች ውል ከተዋዋሉበት ቀን ጀምሮ በአስር የስራ ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት የማስጫያና ማውረጃ ወጪ በመክፈል በሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለቀረቡት እቃዎች ሳምፕል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ከጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ የዋስትና ደብዳቤ ለምታመጡ ድርጅቶች በምትወዳደሩበት ዘርፍ የራሳችሁ ምርት(አምራች) መሆናችሁን የሚገልፅ መረጃ በማቅረብ በአመረታችሁት እቃ ላይ ብቻ የምትወዳደሩ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ት/ቤቱ አሸናፊ ተጫራች ከመረጠ በኋላ በሚገዙት እቃዎች ብዛት እና መጠን ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 30% /ሰላሳ ፕርሰንት የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የተጠቀሰውን ብር በመመርያው መሰረት ከታወቀ ባንክ የጨረታ ማስከበሪያ በCPO በት/ቤቱ ስም በማሰራት ከጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርቸዋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የግዥ አይነት |
ሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
0.5-2% |
|
1 |
የደብ ልብስ |
1 |
22,000 |
1% |
|
2 |
የትምህርትና የቢሮ አላቂ እቃዎች |
2 |
20,000 |
1% |
|
3 |
የፅዳት እቃዎች |
3 |
15,000 |
2% |
|
4 |
ቋሚ እቃ |
4 |
22,000 |
1.7% |
|
5 |
የስፖርት እቃዎች |
5 |
7,000 |
1.5% |
|
6 |
ልዩ ልዩ እቃዎች |
6 |
8,000 |
1% |
አድራሻ፦ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠና ተራ ድልዲይ ስር ወደ ፍሊጶስ በሚወስደው መንገድ 20 ሜትር ገባ ብሎ
ስልክ፡011-280-42-34/35
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የሚሊንየም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት