በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የኮፈሌ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ለመ/ቤቶች የሚውል እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የኮፈሌ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ለመ/ቤቶች የሚውል እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 01, 2026)

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የኮፈሌ ከተማ ገ/ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ለመ/ቤቶች የሚውል

  • 1.የጽህፈት መሳሪያችና ሌሎች የቢሮ እቃዎች 
  • 2. ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • 3. የሰራተኞች የደንብ ልብስ
  • 4. የጽዳት እቃዎች
  • 4.መጋረጃዎች እና ምንጣፍ
  • 5. ፈርኒቸሮች
  • 6. የመኪና ጎማ
  • 7. ሞተር ሳይክል
  • 8. የቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያ የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎችን ይጋብዛል።

1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።

2. ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ግዥ ስለመሳተፍ የሚገልጽ ከህጋዊ አከል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀትማቅረብ አለበት።

3. ተጫራቾች በሚሰሩበት የንግድ ስራ ዘርፍ ትክክለኛ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው።

4. ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ የሚውል ብር 10000/አስር ሺህ/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለበት። ነገር ግን የማይክሮ ድርጅት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሚመለከት የዋስትና ደብዳቤ ህጋዊነት ከአደራጃቸው አከል ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 18/1/2019 እስከ 11፡30 የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ።

6. የሰነዱ ሸያጭ የሚቆይበት ቀን 27/12/2018–18/1/2019 በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 ይሆናል።

7.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በቀን 19/1/2019 2:30 ሰዓት እስከ 4፡30 በቢሮ ቁጥር 4 ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8. ጨረታው በዚያኑ ቀን 19/1/2019 በ 4፡30 በታሽጎ በዚያኑ ቀን በ 5፡00 ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮፈሌ ከተማ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል።

9. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ሙሉ አድራሻቸውን ጽፈወ መፈረምና ማህተም ማድረግ አለባቸው።

10. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ እስከ ኮፈሌ ከተማ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረሰ በራሱ ወጪ በማምጣት ማስረከብ አለበት።

11. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታች ማሻሻል መቀየር እንዲሁም ሃሳቤን ቀይሪያለሁ ማለት አይቻልም።

12. አሸናፊ ድርጅቶች ከሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ማስያዝ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት።

13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙለ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 18 99 60 72/ 09 16 35 88 94 ኮፈሌ ከተማ ገ/ኢ/ል/ ጽ/ቤት ጨረታው የሚከፈተው የበአል ቀን ላይ ከዋለ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል።

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን የኮፈሌ ከተማ
ገ/ጽ/ቤት