የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት 4ኛ ፍትሐብሔሮች ስፋቱ 201 ካ.ሜ የሆነ ቤት መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት 4ኛ ፍትሐብሔሮች ስፋቱ 201 ካ.ሜ የሆነ ቤት መሸጥ ይፈልጋል


Melekite Dire (Aug 26, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት አብዱለዚዝ መሀመድ አቡበከር እና በፍ/ባለዕዳ አቶ አብዱረዛቅ መሀመድ መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክስ ጉዳይ በመዝገብ ቁጥር 85462 የተሰጠውን ውሣኔ ለማስፈፀም በድሬዳዋ ከተማ ዙሪያ በቦረን ደጀን ገጠር ቀበሌ አስተዳደር ክልል ውስጥ በምስራቅ ባዶ ቦታ በምዕራብ የእግር መንገድ በደቡብ ስፋ ኑረዲን እና በሰሜን ወይንሸት ተፈራ የሚያዋስኑት ስፋቱ 201 ካ/ሜ የሆነ በኮርድኔት X-809738 Y-1063476 የሆነ የፍርድ ባለዕዳ የሆነ ቤትና ይዞታ በመነሻ ዋጋ 1,454,472.31 /አንድ ሚሊዮን አራት መቶ ሃምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ሰባ ሁለት ብር 31/100/ በሆነ ዋጋ በሃራጅ ሽያጭ እንዲሸጥ የታዘዘ በመሆኑ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም በጨረታ አወዳድሮ በሀራጅ መሸጥ አስፈልጓል፡፡  ስለሆነም በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 4፡30 ድረስ ባለው ጊዜ የተጫራቾች ምዝገባ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ የሚካሔድ ሲሆን ጨረታው በተጠቀሰው ቀን እና ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ከጠዋቱ 4፡40 እስከ 5፡30 ባለው ጊዜ ይከናወናል፡፡ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ መታወቂያ በመያዝ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ በመገኘት መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ማንኛውም ተጫራች ለሃራጅ ጨረታው ከመዝገቡ በፊት የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ቀድሞ በCPO በባንክ አስይዘው እንዲመዘገቡ በCPO ያልያዘ ተጫራጭ እንዳይመዘገብ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ

የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ያሸነፉበትን ገንዘብ 1/4ኛውን ወዲያውኑ በCPO ወይም በሞዴል 85 በፍ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ማስያዝ አለባቸው፡፡ ቀሪውን 3ኛ ገንዘብ ደግሞ ጨረታው በተካሔደ በ15 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህ ባይሆን ቀድሞ የተያዘው ገንዘብ ለጨረታ የወጣው ወጪ ተቀንሶለት ቀሪው ለመንግስት ገቢ እንደሚሆን ሊገነዘቡ ይገባል፡፡

የድሬዳዋ ምድብ የፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት 4ኛ ፍትሐብሔሮች

ስልክ Tel. ፡- 011-869 44 41

ፋክስ Fax.፡- 011-276 75 78

ፖ.ሣ.ቁ PO Box፡- 8389


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *