Melekite Dire (Aug 26, 2026)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሚኒባስ መኪና ኪራይ የጨ/መ/ቁ/መ/ል/ማ/ቢ – 0003/2019
የድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለ2019 በጀት ዓመት ለቢሮ ሰራተኞች ሰርቪስና ለቢሮ የመስክ ሥራ የሚያገለግለው የሚኒባስ መኪና ኪራይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል በመሆኑም በዘርፉ የተሰማሩ አቅቢዎች /ተጫራቾች እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. በዘርፉ ለ2019 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ት
2. የግብር ከፋይነት የንግድ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያለው/ት
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው/ት
4. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት
5. በዘርፉ የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
6. በድርጅቱ /በባለቤቱ ስም በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የታተመ ቁጥር ያለው ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል
7. የብቃት ማረጋገጫ በድሬደዋ መንገድ ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክ አገልግሎት ባለስልጣን የተረጋገጣ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
8. የተሸከርካሪው መድን ዋስትና (ሶስተኛ ወገን) ያለው ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
9. ተቋሙን የሚመጥን ደረጃ ሁለት (2) ሚኒባስ መኪና ማቅረብ የሚችል
10. አንድ ዓመትና ከዛ በላይ የመልካም ሥራ አፈጸጸም ማስረጃ መቅራብ የሚችል
11. የጨረታ ማስከበሪያ/CPO/ በባንክ የተረጋገጠ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር) ማቅረብ የሚችል ከላይ የተጠቀሰውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በድሬዳዋ አስተዳደር መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 303 በመቅረብ የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለጨረታው በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ።
12 ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 303 3ኛ ፎቅ ይከፈታል፡፡
በ16ኛው ቀን በዓል፣ ቅዳሜና እሁድ ቀኑ ከዋላ በሚቀጥለው የሥራ ቀናት የሚከፈት ይሆናል፡፡
ቢሮው የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡– በስልክ ቁጥር 09-20-42-33-92 / 09-10-25-82-50 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በድሬዳዋ አስተዳደር የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ
የግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት