Addis Zemen (Sep 04, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2109 ዓ.ም.
የአጋዝያን ቁ.3 2ኛ ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚከተሉት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- አላቂ የት/ት እቃዎችን፣
- አላቂ የጽዳት እቃዎችን፣
- የደንብ ልብስ፣
- የቢሮ እቃዎች፣
- የፎቶ ኮፒ ቀለሞች፣
- የስፖርት እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ እንዲሁም የንግድ መለያ ቁጥር (Tin number) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ የንግድ ምዝገባ ማስረጃ ያላቸውና በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ።
- የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በመንግሥት ጨረታ ላይ የመሳተፍ ጊዜ ያላለፈበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያገለግሉ የሚጫረቱበትን የዕቃ ዋጋውን ብር 10,000.00/አስር ሺህ ብር/ በጽሕፈት ቤቱ ስም የተዘጋጀ /ሲፒኦ/ወይም በጽሕፈት ቤቱ ፋይናንስ በካሽ በማስያዝ ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያው ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የምታስገቡቸው ሰነዶች ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሊኖረው አይገባም፣ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ውድቅ ነው የሚሆነው።
- የጨረታው ተሳታፊዎች የሚያቀርቡበትን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጂናሌና ኮፒ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለፅ የእቃ ብዛት የመጨመርም ሆነ የመቀስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው የሚሰሩ ነጋዴዎች የድጋፍ ደብዳቤ ስታመጡ ደብዳቤው በጽ/ቤቱ ኃላፊ ቲተርና ፊርማ ተፈርሞ ማምጣት ግዴታ ነው።
- ከላይ የተጠቀሱት እቃዎች ዝርዝር የሚያሳውቅና የግዥ መመሪያ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፋ/ግ/ን/አ/ጽ/ቤት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዝርዝር የተጻፈ ሰነድ በአጋዝያን ቁ.3 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ ጋዜጣው በወጣበት በ11ኛው /በአስራ አንደኛው የሥራ ቀን ጨረታው በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአጋዝያን ቁ.3 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል፡፡ መሥሪያ ቤቱ የተሻለ የግዥ ዘዴ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው መሰረዝ ይችላል።
አድራሻ፡– ጎጃም በረንዳ /ሀግቤስ/ አቢሲኒያ ባንክ አጠገብ
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡– 0111-11-01-23 /0111-11-42-10 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአራዳ ክፍል ከተማ ት/ጽ/ቤት የአጋዝያን ቁ.3 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራሂደት