ኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሸገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከጅማ ዞን ከሚገኘው ከጢሮ አፈታ ልዩ ስሙ /አገሎ/ ደን እስከ ፊንፊኔ (አ/አ) ድረስ ደን ውስጥ የተዘጋጀውን የጽድ ግንድ ለማጓጓዝ የጭነት መኪናን በጨረታ አወዳድሮ ለማስጫን ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሸገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከጅማ ዞን ከሚገኘው ከጢሮ አፈታ ልዩ ስሙ /አገሎ/ ደን እስከ ፊንፊኔ (አ/አ) ድረስ ደን ውስጥ የተዘጋጀውን የጽድ ግንድ ለማጓጓዝ የጭነት መኪናን በጨረታ አወዳድሮ ለማስጫን ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 06, 2026)

የጭነት መኪና ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 005/2018/19

ድርጅታችን ከጅማ ዞን ከሚገኘው ከጢሮ አፈታ ልዩ ስሙ አገሎ/ ደን እስከ ፊንፊኔ (አ/አ) ድረስ ደን ውስጥ የተዘጋጀውን የጽድ ግንድ ለማጓጓዝ የጭነት መኪናን በጨረታ አወዳድሮ ለማስጫን ይፈልጋል።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው።

1. በዘርፉ የተሰማራችሁ ሁሉም ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ከፌዴራል ከክልል ትራንስፖርት ባለስልጣን የታደሰ የጭነት አገልግሎት የደረጃ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸው እና ኮፒውን ማቅረብ የምችሉ።

2. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት (የምስክር ወረቀትና) የታደስ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።

3. ጊዜው ያላለፈበትን በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ነፃ የምስክር ወረቀት (Tax clearance certificate) ማቅረብ የሚችል፡፡

4. ተጫራች ድርጅቶች የቴክኒካልና የፋይናንስ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራች ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ የተጫረቱበትን 5% በ cpo ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሸገር ቅርንጫፍ በሚል ስም በማሰራት ከቴክኒካል ፖስታ ጋር ለብቻው በማቅረብ መጫረት ይችላሉ።

6. ማንኛውም ተጫራቾች ሌላው ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።

7. ተጫራች ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

8. ከጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመኖራቸው የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

የጨረታ ሠነዱን ለቡ መብራት ኃይል ሮያል ከረሜላና ቸኮሌት ፋብሪካ ህንጻ 3ተኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው ቅርንጫፍ ጽ/ቤታችን ከሰኞ እሰከ አርብ በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ከፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ቅዳሜ እሁድና የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል፡፡ መ/ቤቱየተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912080221 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ሸገር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *