የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል


Reporter (Sep 06, 2026)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ቀጥሎ የተመለከተዉን ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።

ተቁ

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

ቅርንጫፍ

          የንብረቱ መለያ ቁጥርና አድራሻ

የጨረታው መነሻ ዋጋ

ሐራጅ የሚከናወንበት

 

 

ከተማ

ወረዳ/ቀበሌ

 

ካርታ ቁጥር

የቦታው ስፋት(.)

የጨረታው ደረጃ

 

ቀን

ሰዓት

 

1.

ሐዋስ ቡሎ ሚደክሶ

ሐዋስ ቡሎ ሚደክሶ

አለምጤና

አለምጤና

ኦዳ

WBIFLMB/3419/AL/2006

400 .

2,631,544.16

26/01/2019 .

ጠዋት 400- 600

5 ዙር

 

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች፡-

  1. በጨረታው እለት የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ መወዳደር ይችላሉ፤ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ ተመራጭ ነው።
  2. ጨረታው የሚካሀደው አዳማ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ውስጥ ሲሆን ስለ ሚጫረቲት ንብረት ከቅርንጫፍ ባንኩና ከአዳማ ዲስትሪክት ሕግ አገልግሎት ተገቢውን ማብራሪያ ማግኘት ይቻላሉ።
  3. በጨረታው ለተሸነፉት ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል።
  4. የጨረታው አሸናፊ በ15 ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ ከፍሎ ማጠናቀቅ አለበት።
  5. የጨረታው አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያውን ካላጠናቀቀ ጨረታውን በፍቃዱ እንዳፈረሰ ተቆጥሮ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  6. የጨረታው አሸናፊ የገዛውን ንብረት የስም ማዘዋወሪያ እና ማንኛውንም ወጪ ሁሉ እራሱ ይከፍላል።
  7. በህግ ገዢ እንዲከፍል የተወሰኑ ማንኛውንም ታክሶች፤ግብሮች ከስም ዝውውር የተያያዙ ክፍያዎች በጨራታ የአሸናፊ የሆነው ገዢ ይከፍላል።
  8. ንብረቱ ለገዢው ስም እንዲዛወር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ማረጋገጫ ይጽፋል።
  9. የንግድ ማህበራታን ወክሎ ለመጫረት የማህበራቱን መመስረቻ ጽሁፍ እና መተዳደርያ ደንብ የያዘና በማህበራቱ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።
  10. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊል ሆነ በሙሉ የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ሶሬቲ ሲቲ ሞል 2ኛ ፎቅ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ሕግ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 17 ማነጋገር ይቻላል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዳማ ዲስትሪክት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *