ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግል ማህበር የከብትና እና የዶሮ ተረፈ ምርቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃ.የተ.የግል ማህበር የከብትና እና የዶሮ ተረፈ ምርቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 08, 2026)

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር EL-LS-2026-083

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ .የተ.የግል ማህበር ከዚህ በታች የተገለጹትን የከብትና እና የዶሮ ተረፈ ምርቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

/ ( ኮድ)

የምርቱ ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ .. (CPO)

የምርት መረከቢያ ቦታ

ሎት 1

የዶሮ ተረፈ ምርቶች (የዶሮ ጉሮሮ፣ መጫጫሪያ፣ጉበት፤ልብ መቋደሻ ፣ቆዳና አጥንት) እንዲሁም የዶሮ ፍግ

100,000.00

ደብረዘይት ዶሮ ምርት ኦፕሬሽን

ሎት 2

ከእርድ የሚወጣ የከበት ተረፈ ምርት (የበሬ እና የበግ ሆድዕቃ እና ሌሎች ተረፈ ምርቶች)

100,000.00

ደብረዘይት ኤክስፓርት ቄራ

ሎት 3

ከእርድ የሚወጣ የከበት ተረፈምርት (የበሬ ሆድ ዕቃ እና ሌሎች ተረፈ ምርቶች)

100,000.00

ኮምቦልቻ ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ

ሎት 4

ከእርድ የሚወጣ የከበት ተረፈምርት (የበሬ ሆድ ዕቃና እና ሌሎች ተረፈ ምርቶች)

100,000.00

መልጌ ወንዶ ምግብ ማቀነባበሪያ

ሎት 5

ከእርድ የሚወጣ የከበት ተረፈምርት (የበሬ ሆድ ዕቃና  እና ሌሎች ተረፈ ምርቶች)

100,000.00

ጎንደር ምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡

1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ወይም የቲኦቲ ተመዝጋቢ የሆኑ መጫረት ይችላሉ፤

3. ተጫራቾች አዲስ አበባ ላይ የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን ከጉርድ ሾላ ከሚገኘው ዋና /ቤት መግዛት ይችላሉ፤ የጨረታ ሰነዱ መግዣ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ) ነው፡፡

4. ተጫራቾች በገዙት ዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ላይ በተዘረዘረው እና በተያያዘው መሠረት መጫረት ይችላሉ፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የለበትም፡፡

6. ማንኛውም ተጫራች ለተረፈ ምርቱ ሲወዳደር ከላይ በሰንጠረዡ የተገለፀውን ብር መጠን የጨረታ ማስከበሪያ .. ( CPO) ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

7. ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ ይደረጋል፡፡

8.ተጫራቾች ለጨረታ የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ በተራ ቁጥር 1 እና 2 የተገለጹትን ፎርማሊቲዎች በሟሟላት በዚሁ ፖስታ አሸገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን መለያ ኮድ (ሎት) እና ቦታ በፓስታው ላይ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡

10. ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅዳሜና እሁድን ሳይጨምር 7 (ሰባት) የሥራ ቀናት በኤልፎራ ዋናው /ቤት 4 ፎቅ ገበያና ሽያጭ አገልግሎት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ፖስታቸውን እንዲያስገቡ ይደረግና፤ በስምንተኛው ቀን ከቀኑ 730 ሰዓት የጨረታው ሣጥን ይታሸጋል፡፡ ከዚያም በዚሁ ዕለት 800 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ ውስጥ ጨረታው ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለ መረጃ፡በስልክ ቁጥር፤ +251 911 172 601 / +251 954 495 363

ኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ .የተ.የግል ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *