የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 08, 2026)

ሀገር አቀፍ የግልጽ ረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ 2019 በጀት ዓመት ለሁሉም የዞን መምሪያዎችና ተጠሪ /ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1 የጽ/መሳሪያ
  • ሎት 2 ቋሚ አላቂ
  • ሎት 3 የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
  • ሎት 5 የፈርኒቸር እቃዎች
  • ሎት 6 የፖርሳ ዘሮች
  • ሎት 7 ምንጣፍ እና መጋረጃ
  • ሎት 8 የስፖርት እቃዎች
  • ሎት 9 የመኪና እቃዎች
  • ሎት10 የመኪና ባትሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የግበር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ያላቸው
  3. የታክስ ክሪላንስ ማቅረብ የሚችል
  4. የግዥ መጠኑ 500,000.00/አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮን ከማጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
  6. ማንኛውም ተጫራች ኦርጅናል እቃ መሙላትና ያሸነፉባቸውን እቃዎች ከባለሙያ ማስፈተሸና ማረጋገጥ አለባቸው፤
  7. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  8. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ዋጋ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የእቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው።
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር /300/ ሶስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል ከፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 601 ማግኘት ይችላሉ።
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ለሎት 1 ብር 80,000.00(ሰማንያ ሽህ ብር ብቻ ) ፣ለሎት 2 ብር 20,000.00( ሀያ ሽህ ብር ብቻ ፣ለሎት 3 ብር 50,000.00(ሀምሳ ሽህ ብር ብቻ)፣ለሎት 4 ብር 100,000.00(አንድ መቶ ሽህ ብር ብቻ )፣ለሎት 5 ብር 80,000.00(ሰማንያ ሽህ ብር ብቻ )፣ለሎት 6 ብር 55,000.00( ሀምሳ አምስት ሽህ ብር ብቻ ለሎት 7 ብር 30,000.00(ሰላሳ ሽህ ብር ብቻ) ሎት 8 ብር 50,000.00(ሀምሳ ሽህ ብር ) ለሎት 9 ብር 10,000.00(አስር ሽህ ብር ብቻ) ለሎት 10 ብር 50,000.00(ሀምሳ ሽህ ብር ብቻ) በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸዉ የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደተጫራች ምርጫ ሲፒኦ /CPO/ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና 73 ቀን ያላነሰ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ማስያዝ አለባቸው።
  11.  የጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት 10% ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
  12. ውድድሩ የሚካሄደው በእቃዎቹ አይነት በሎት ጠቅላላ ድምር ነው
  13. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዚጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
  14. ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገንዘብ መምሪያ አዳራሽ 6 ፎቅ በ11ኛው ቀን ከጧቱ 400 ሰዓት ታሽጎ 430 ላይ ይከፈታል የመክፈቻው ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ 430 ላይ ይከፈታል።
  15. በጨረታ ለማሳተፍ ለሚፈልጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 610 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033111 81 18/19 ማግኘት ይችላሉ።
  16.  አሸናፊው ድርጅት ያሸነፉትን እቃ ደቡብ ወሎ ዞን ባሉ 4 የፑል ንበረት ክፍሎች ገቢ ማድረግ አለባቸው።
  17. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ድምር ካላስቀመጡ ከውድድር ውጭ ይደረጋሉ።
  18. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ላይ የአንድ ዋጋም ጠቅላላ ዋጋም ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ይደረጋል።
  19. እቃዎቹ ሳምፕል የተቀመጡ ስለሆነ የጨረታ ሰነድ ሲገዙ ሳምፕሉን ይመልከቱ
  20. ተጫራቾች የጨረታ መመርያ፣የተጫራቾች ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ እና የግምገማ ዘዴና መስፈርት በሶፍት ኮፒ መውሰድ ይችላሉ
  21. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የደቡብ ወሎ ገንዘብ መምሪያ