Addis Zemen (Sep 09, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001
በየካ ከፍለ ከተማ በወረዳ 10 ት/ጽ/ቤት ዳንሴ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት የ2019 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1፣ የደንብ ልብስ፣
- ሎት 2 የፅህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት 3 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- ሎት 4 የፅዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 5 የጥገና እቃዎች፣
- ሎት 6 የኤሌክትሪክ ቋሚ እቃዎች፣
- ሎት 7 የተገጣጣሚ ቋሚ እቃዎች
በዚህ መሰረት በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- በዘርፉ የተሰማሩ የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ
- የዘመኑ ግብር አጠናቀው የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል ።
- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል የሚመለስ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ብር በእያንዳንዳቸው
- ሎት 1 ብር 12900.00 (አስራ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር ብቻ)፣
- ሎት 2 ብር 8200.00 (ስምንት ሺህ ሁለት ብር ብቻ)፣
- ሎት 3 ብር 9700.00 (ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ብር ብቻ)፣
- ሎት 4 ብር 6700.00 (ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ብር ብቻ)፣
- ሎት 5 ብር 2000.00 (ሁለት ሺህ ብቻ)፣
- ሎት 6 ብር 8000.00 (ስምንት ሺህ ብር ብቻ)፣
- ሎት 7 ብር 5000.00(አምስት ሺህ ብር ብቻ) ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ዝርዝር ጨረታውን የያዘውን ሰነድ የማይመለስ ሶስት መቶ /400.00 ብር በመክፈል በዳንሴ ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የፋይናንስ ድጋፍ የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን እቃ ናሙና ለሚያስፈልገው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ሳምፕል ለማምጣት አስቸጋሪ ከሆነ በፎቶ ማቅረብ ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ አሸንፈው ውል ሲዋዋሉ የአጠቃላይ ብር 10% ውል ማስከበሪያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሰነድ ኮፒና ኦርጅናል በመለየት በተለያየ ፖስታ አሽገው ሲመጡ ሲፒኦ ደግሞ የጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ባለበት ፖስታ ውስጥ በማስገባት አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ዝርዝር ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረብ በግልጽ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ድረስ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ ከወጣበት በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን 4፡30 በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው
በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል
ማለት ነው፡፡ - መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ፈረሳይ ጉራራ 12፣ 55፣ 64 ማዞሪያ ኪዳነምህረት በስተጀርባ ዳንሴ አንቆርጫ ፖሊስ ሴተር ጎን ዳንሴ ቅ/አ አ/መ/ደ/ት/ቤት
ስ.ቁጥር 0941262266/0962862755
በየካ ክፍለ ከተማ በወረዳ 10 ት/ጽ/ቤት
የዳንሴ ቅ/አ/አ/መ/ደ/ት/ቤት