ዑመማፍ የአረጋውያን እና ሕጻናት መርጃ ድርጅት የ2018 የበጀት ዓመት የፋይናንስ የሥራ ከንውን በቻርተር የተመሰከረለት የሂሳብ አዋቂ እና የተፈቀደለት የውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ዑመማፍ የአረጋውያን እና ሕጻናት መርጃ ድርጅት የ2018 የበጀት ዓመት የፋይናንስ የሥራ ከንውን በቻርተር የተመሰከረለት የሂሳብ አዋቂ እና የተፈቀደለት የውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 09, 2026)

የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ

ናዝሬት አዳማ የሚገኘው ዑመማፍ የአረጋውያን እና ሕጻናት መርጃ ድርጅት 2018 የበጀት ዓመት የፋይናንስ የሥራ ከንውን በቻርተር የተመሰከረለት የሂሳብ አዋቂ እና የተፈቀደለት የውጭ ኦዲተር ለማስመርመር ይፈልጋል፤

ስለሆነም ከዚህ በታች ተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ኦዲተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ሰነዳችሁን በታሸገ ፖስታ በማድረግ እና የድርጅቱን ማህተም በመምታት በአካል በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት በኋላ የሚመጡ ተወዳዳሪዎች በድርጅቱ ተቀባይነት እንደሌላቸው እናሳውቃለን፡፡

ተወዳዳሪዎች ማሟላት ባቸ መስፈርቶች

1. የታደሰ የንግድ የስራ ፍቃድ

2. የሙያ ማረጋገጫ ፍቃድ

3. TIN (የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር)

4. Vat/TOT ሰርተፍኬት

5. ስራውን ሰርቶ ለማቅረብ የሚፈጅበት የጊዜ ገደብ እና

6. የገንዘብ መጠን በግልጽ መታየት (መቀመጥ) አለበት፡፡

አድራሻ፡በኪዳነምህረት /ክርስቲያን በኮብልስቶኑ ገባ ብሎ ፖሊስ ጣቢያው ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር፡ 0927 326 543 / 0919 649 295

ዑመማፍ የአረጋውያን እና ሕጻናት መርጃ ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *