የተሽከርካሪ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የተሽከርካሪ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Sep 09, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት አፍሪካ ሴክስ ኢትዮጵያ /የተ/የግ/ እና የፍ/ባለዕዳ ጥበብ ኮንስትራክሽን /የተ/የግ/ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ /ቤት በመ/ቁጥር/240308 9/5/2015 . እና በኮ///268355 18/03/2018 . በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአራዳ /ከተማ ወረዳ 06 በከሳሽ ድርጅት ግቢ ውስጥ ቆሞ የሚገኝ እድሳትና ጥገና የሚፈልግ ሬንጀር 4 ሰው 7 ኩንታል የሚጭን የሰ/ቁኮድ 3-18392 አአ ተሸከርካሪ በጉሙሩክ ኮሚሽን የቀረጥ ታክስ ዕዳ የሌለበት ሆኖ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 643,104 (ስድስት መቶ አርባ ሶስት ሺህ አንድ መቶ አራት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ መስከረም 28 ቀን 2019 . በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 500 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም /ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ//ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም /ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ 330 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትየጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ 1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ//ቤት ስም CPO አሠርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን 15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ//ቤት በሕጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 112 730 852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌዴራ ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም /ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *