Reporter (Sep 09, 2026)
የፐብሊክ ኦዲተር የሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
ንቁ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር (Niqu SACCOS) የአባትን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ቀልጣፋ የብድርና የቁጠባ አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም ሲሆን፣ ፍላጎት ያላቸውን የፐብሊክ ኦዲት ድርጅቶች ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 3 አመት በየ3(ሶስት) ወሩ የበጀት ዓመታት የማኅበሩን ሂሳብ ኦዲት እንዲያደርጉ ይጋብዛል።
በመሆኑም በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የፐብሊክ ኦዲተር ፍቃድ የተሰጣቸው ተቋማት ብቻ
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የቫት ምዝገባና የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- በኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ የታደሰ የምዝገባ ፈቃድ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል ተቋም!
- በሥራው ላይ በተለይም የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት (SACCOS) ኦዲት በማድረግ በቂ ልምድ ያለው
- የአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት የተከተለ ሂሳብ ኦዲት ያደረገና ልምድ ማቅረብ የሚችል!
- አግባብነት ያለው የኅብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅና መመሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ የኦዲት ተቋም
- የሚቀርበው የጨረታ ዋጋ ከ2019-2021 ዓ.ም ድረስ ያለውን የሶስቱንም ዓመት (በየሶስት ወሩ የሚሰራውን ጨምሮ) ያካተተ መሆን ይኖርበታል።
ንቁ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር (Niqu SACCOS) ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስለሆነም ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በዋናው መስሪያ ቤታችን በአካል በመቅረብ የሚሰሩበትን ዝርዝር ማብራሪያውንና ዋጋ (Technical and Financial Proposal) ከአስፈላጊ ሰነዶች ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን TOR እና የጨረታ ሰነድ በተጠቀሱት ቀናት ዋናው ቢሮ በመቅረብ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ንቁ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበር (Niqu SACCOS)
ዋና አድራሻ፡- ንቁ አባዶ ቅርንጫፍ። የካ አባዶ ንደራ፣ ባጫ ሞል፣ 3ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር፡- 09 73 77 47 44 / 09 56 50 50 99 / 09 56 50 50 61
ኢሜል፡- Niqusaccos168@gmail.com በንቃት ለሚተጉ እጆች