2merkato.com (Sep 10, 2026)
አበባ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግ.ማ.
የጽዳት እና የጥበቃ አገልግሎት ጨረታ ማስታወቂያ
አበባ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግ.ማ. በጎተራ የሚገኘውን ዋና መሥሪያ ቤትና ጋራዥ እንዲሁም በጉርድሾላ የሚገኘውን ጋራዥ የጽዳት እና የጥበቃ አገልግሎት ለሁለት ዓመት በውጭ ድርጅት ለማሰራት በጨረታ ብቃት ያላቸውን የጽዳትና የጥበቃ አገልግሎት ድርጅቶች ይጋብዛል።
የአገልግሎቱ ወሰን
1. የጥበቃ አገልግሎት
Ø ጎተራ ዋና መሥሪያ ቤትና ጋራዥ፡ 9 የጥበቃ ሠራተኞች (8 ወንድ፣ ከነዚህ 1 ሱፐርቫይዘር፣ እና 1 ሴት የቀን ቁጥጥር/ፍተሻ)።
Ø ጉርድሾላ ጋራዥ፡ 6 ወንድ የጥበቃ ሠራተኞች፣ ከነዚህ 1 ሱፐርቫይዘር።
Ø የጥበቃ አገልግሎቱ 24 ሰዓት በሶስት ፈረቃዎች ይሰጣል።
2. የጽዳት አገልግሎት
Ø በጎተራ ዋና መሥሪያ ቤት ብቻ 4 ሴት የጽዳት ሠራተኞች በአንድ ፈረቃ የሚሰሩ ይሆናሉ።
የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ
ፍላጎት ያላቸውና በዘርፉ ሕጋዊ ምዝገባ ያላቸው ድርጅቶች የሕጋዊነት፣ የቴክኒክ ብቃት፣ የተመሳሳይ ሥራ ልምድ እና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን ከዋጋ ማቅረቢያቸው ጋር በማቅረብ መሳተፍ ይችላሉ።
የጨረታ ዋስትና፡ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% በCPO ወይም በባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) መሆን አለበት።
የጨረታ ጊዜ፡ ጨረታው ከመስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም. (09/09/2026) ጀምሮ ለ15 ቀናት ክፍት ይሆናል። የመዝጊያ ቀን፡ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም. (23/09/2026)።
የጨረታ ሰነዱንና ተጨማሪ መረጃዎችን ከአበባ ትራንስፖርት ዋና መሥሪያ ቤት ጎተራ፣ ከፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው ጽ/ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 200 ከፍለው ማግኘት ይቻላሉ።
አበባ ትራንስፖርት ኃ.የተ.የግ.ማ.
ሰው ሀብት እና ጠቅላላ አገልግሎት መምርያ
ስልክ፡ +251965108202