የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት እቃ፣ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ እስፔርፓርት፣ የፅዳት እቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሐራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣ የቤት ማስዋቢያ፣ የቤት እቃ፣ ኮንስትራክሽን፣ አልባሳት፣ እስፔርፓርት፣ የፅዳት እቃ፣ ምግብ ነክ እና ልዩ ልዩ በሐራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 10, 2026)

ግልፅ የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጉምሩክ ኮሚሽንጅግጅጋቅ/ጽ/ቤት በኮንትሮባንድ የተያዙ

  •  የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ፣
  • የቤት ማስዋቢያ
  • የቤት እቃ
  •  ኮንስትራክሽን፣
  •  አልባሳት፣
  •  እስፔርፓርት፣
  •  የፅዳት እቃ ምግብ ነክ እና
  •  ልዩ ልዩ በሐራጅ እና በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን እቃዎች 05/01/2019 ጀምሮ ሳምፕል በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል፡፡

ስለሆነም በጨረታው ላይ ለመካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች:-

  1. በዘርፋ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ፣
  2. ለሐራጅ ጨረታው 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ማቅረብ የሚችል፤
  3. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ እቃውን ለመግዛት የሚያቀርበውን የመጫረቻ ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ሲፒኦ (CPO) ማቅረብ የሚችል፤
  4. ለሐራጅ ጨረታ ተጫራቹ የሚገዛበትን መነሻ ዋጋ እራሱ ያቀርባል፤
  5. ለግልፅ ጨረታ ቅ/ጽ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፤
  6. ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን እቃ ከፍያውን በዐ5 ቀናት ውስጥ መፈፀም አለበት፤
  7.  እቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ለመንግስት ገቢ ይሆናል፤
  8. በጨረታው ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፤
  9. አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል፤
  10. ማንኛውም ተጫራች እቃዎቹን ካሸነፈ በኋላ ከጅግጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደየቦታው እርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል፤
  11. ተጫራቹ እቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፤
  12. ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ከቀን 05/01/2019 ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ቅ/ጽ/ቤት የእቃ አወጋገድ ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው በዐ7/01/2019 3:45 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ 4:00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤
  13. የሐራጅ ጨረታው የሚካሄደው 07/01/2019 ከጠዋቱ 4፡15 በመሰብሰቢያ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል፤

N.B፦ አሸናፊ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% (አስራ አምስት ፐርሰንት)

የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ፤ ሳምፕል ሳያዩ የሚጫረቱ ተጫራቾች ቅ/ጽ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡

በጉምሩክ ኮሚሽን ጅግጅጋ ቅ/ጽ/ቤት