Addis Zemen (Sep 12, 2026)
በጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች የሀራጅ ጨረታ ቁጥር ሐ13/2019 ጨረታ
በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 አንቀፅ 13 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት አስመጭዎች ዕቃቸውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የጉምሩክ ሥነ–ሥርዓት ፈጽመው ባለመውሰዳቸው ዕቃዎቻቸው እንደተተው የተቆጠሩ እና በተለያየ ምክንያት የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት – በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም TOYOTA OIL FILTER HIK VISION SOLID STATE DRIVES, HDD SEAGATE & COMPUTER RAM DAF TRACK VAN CAR WITH CONTAINER AUTOMATIC VOLTAGE REGULATOR CHILDREN FROCK, BABY FROCK & OTHER COMPLETE SET DOUBLE LEAF STEEL FIRE RATED DOOR LABORATORY STOOL CHAIR PERFUME HAIR CLIPPER, VACUUM FLASK, CHEWING GUM & CHOCOLATE የተለያዩ አልባሳት ጫማዎችና ሌሎች እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1) ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፤ ዓይነት እና ብዛት በማስታወቂያ ሠሌዳ እና በአካል ለመመልከት ከቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግቢ ሃሳቦች ቡድን ሰነድ በመግዛት ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ሰዓት መመልከት ይቻላል።
2) ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ
መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ።
N.B: ተሽከርካሪ ላይ ለመጫረት የተሽከርካሪው አስመጭ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ ከሆነ ሰው በስተቀር ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የታደሰ መታወቂያ በማቅረብ ቅድመ ሁኔታዎቹን ማሟላት ሳያስፈልገው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
3) ማንኛውም ተጫራች : ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ዘርፉ በሚፈቅደው ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሽህ ብር) ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ ጽ/ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFIC በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፤ አዳማና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት።
4) የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ በ8ኛው የሥራ ቀን በዚሁ ዕለት ጠዋት 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ የሚከፈት ሆኖ
5) ማንኛውም ተጫራች አስከ 4፡45 ሰዓት የሚጫረትበትን ዕቃ ለይቶ እቃ አወጋገድ ቡድን ቀርቦ ማስመዝገብ ይኖርበታል።
6) ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታውን ከአሸነፈ በኋላ እራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይቻልም የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
7) የሐራጅ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ / CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ, ይደረጋል።
8) በተራ ቁጥር 06 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፤ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል።
9) አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል።
10) ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11) ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት