በጂማ ዞን የሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ የእቃ አይነቶች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በጂማ ዞን የሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ የእቃ አይነቶች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 11, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በጂማ ዞን የሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ፡-

  1. የጽሕፈት መሣሪያና አላቂ ዕቃዎች
  2. ፈርኒቸር
  3. ጀኔሬተር
  4. የደንብ ልብስ
  5. የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች
  6. ሞተርሳይክል
  7. የመኪና ጎማ

ስለዚህ በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ፍቃድ ያሳደሱ ስለመሆናቸው ማስረጃቸውን ኦሪጅናልና ፎቶኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታከስ /VAT እና TIN No ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ሰርተፍኬት ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
  3. ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ለእያንዳንዱ የዕቃ ዓይነት ብር 20000 ሕጋዊነቱ ከተረጋገጠ ባንክ በ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ለዚህ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ከሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ 200 ብር በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ በ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች አስፈላጊውን ሰነድ በሙሉ ፎቶ ኮፒውን በአንድ ፖስታ ውስጥ ከተው ኦሪጅናሉን ደግሞ በሌላ አንድ ፖስታ ውስጥ ከተው, technical document በአንድ ፖስታ ውስጥ ከተው ባጠቃላይ በ 3 ፖስታዎች ውስጥ ከተው, ፖስታዎቹን በሰም አሽገው ላዩ ላይ ፈርመውና ማሕተም አድርገውበት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 15ኛው የሥራ ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ መከተት ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው የሥራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች (ሕጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በመሥሪያ ቤታችን የግዥ ከፍል (ቢሮ ቁጥር 3) የሚከፈት ይሆናል።
  8. የተጫራች ሰነዶች ቀርቦ ተጫራች በአካል ባይገኝም ጨረታው ይከፈታል።
  9. አሸናፊ ሆኖ የተገኘ ተወዳዳሪ የሚታዘዘውን ዕቃ በሙሉ ወጪውን ችሎ እስከ መሥሪያ ቤታችን ድረስ የሚያቀርብ ይሆናል።
  10. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የሸቤ ሶንቦ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት