Addis Zemen (Sep 12, 2026)
የ2018 ዓ/ም የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019 ዓ/ም
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጎሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
የሎት ቁጥር |
የዕቃው አይነት |
|
ሎት 1 |
ኤሌክትሮኒክስና ተዛማጅ እቃዎች 6313 |
|
ሎት 2 |
የመዳሐኒት ግዥ 6214 |
|
ሎት 3 |
የፓርቲሽን ስራዎች 6244 |
|
ሎት 4 |
የአላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች 6219 |
|
ሎት 5 |
የጽዳት እቃዎች 6218 |
|
ሎት 6 |
የሰራተኛ ደንብ ልብስ እቃዎች 6211 |
|
ሎት 7 |
የተለያዩ ህትመቶች 6213 |
|
ሎት 8 |
የመኪና ኪራይ 6213 |
ስለሆነም መስፈርቱን ያማሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
1. የአገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
2. የአገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ስብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ/ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የአገር ውስጥ ተጫራቾች የ2019 በጀት ዓመት የታደሰ የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው።
4. የአገር ውስጥ ተጫራቾች የቫት ተመዘጋቢ የሆኑና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
5. ሎት 1 እስከ ሎት 3 መስሪያ ቤቱ ባወጣው /Specification/ መገለጫ የሚቀርብ ይሆናል ከሎት 4 እስከ ሎት 7 የሚወዳደሩ ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የዕቃውን ናሙና በዝርዝር ለግዥ ክፍል ገቢ ማድረግ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል። በተጨማሪም ናሙና ያልቀረቡት የእቃ አይነት ከውድድር ውጭ ይሆናል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ ሎት1– (60000) ስልሳ ሺህ ብር ሎት-2 (30000) ሰላሳ ሺህ ብር፧ ሎት-3 (300000) ሶስት መቶ ሺህ ብር ሎት-4 (10000) አስር ሺህ ብር ሎት-5 (20000) ሀያ ሺህ ብር ሎት-6 (2000) ሀያ ሺህ ብር ሎት-7 (20000) ሀያ ሺህ ብር ሎት -8 (10000) አስር ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /C.PO/ ብቻ ማቅረብ አለባቸው። በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆኑ ከአደራጃቸው አካል መደራጀታቸውንና በጨረታ ስራ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
7. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11 ሰዓት ለእያንዳንዱ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል ጎሮ ሰፈራ ጤና ጢቢያ አዲሱ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር በመውሰድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 1ዐኛው የስራ ቀን 11 ሰዓት ድረስ ጎሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን መውሰድ ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው በታሸገ ኤንቬሎፕ ኮፒና ኦሪጂናል በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በተዘጋጀው ጎሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ በግዥ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎታቸው በተገኙበት በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በጎሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ አቢሲኒያ ባንክ አጠገብ ያለው ፖሊስ ጣቢያ ገባ ብሎ ግዥ ክፍል አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር ይከፈታል።
10. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን እቃዎች በአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የማስያዝና የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
11. በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ከሆኑ ካደራጃቸው አካል መደራጀታቸውንና የጨረታ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
12. ከላይ የተጠቀሱት መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከር ከጨረታው ያሰርዛል።
13. መ/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታው ካቀረበው ብዛት 20% ከፍና ዝቅ ብሎ የግዥ ትዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
14. ለጨረታው የተሰጠው ዋጋ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል
15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጎሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ አቢሲንያ ባንክ አጠገብ ካለው ፖሊስ ጣቢያ ገባ ብሎ አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በአካል በመምጣት ወይም ስልክ ቁጥር 09-81-55-80-30 በመደወል መረጃውን መውሰድ ይችላሉ።
የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጎሮ ሰፈራ ጤና ጣቢያ ግዥ ቡድን