የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


Addis Zemen (Sep 11, 2026)

የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት ካሌብ አገልግሎት ሰጪ ፋርመው ሀውስ ሀ/የተ/የግ/ማህበር እና በፍ/ባለዕዳ ሐዋ አሊ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 115767 በ15/5/2017ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/120964 በ16/10/2017ዓ/ም በኮ/መ/ቁ/120964 በ03/11/2018ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቢሸፍቱ ከተማ አስተዳደር ዲባዩ ክ/ከተማ ደከቦራ ቀበሌ ውስጥ በከሳሽ ድርጅት ግቢ ውስጥ የሚገኝ የሰ/ቁኮድ 3-83785 ኢት የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 5,924,160 ( አምስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ አራት ሺህ አንድ መቶ ስልሳ) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ጥቅምት 4 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ c.PO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ
አፈጻጸም ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *