Be'kur (Sep 14, 2026)
ለአራተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ጐጃም ዞን የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ በመጋዘናችን ውስጥ ከሚገኘው የ2018 ምርት ዘመን የስንዴ ሰብል ውስጥ 5,000 ኩ/ል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ሁሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በኦርጅናል የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት እና ክብ ማህተም በማድረግ የድርጅቱ ማህተም በማድረግ ፓስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት እና ፖስታው ላይ ሶስት ቦታ ማህተም በማድረግና መስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ8 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስከ 8ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ድረስ መግዛትና ማስገባት የሚችሉ፡፡ በ8ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በእለቱ በ8ኛው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ባሉበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው አይስተጓጐልም፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከዩኒየኑ ግዥና ፋይናንስ ዲቪዥን መውስድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የጠቅላላ ዋጋውን 2 በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማያያዝ አለባቸው፡፡
- የንግድ ፈቃዱ ወይም የድርጅቱ ስምና የክብ ማህተሙ ስም ተመሳሳይ መሆን ሲኖርበት እንዲሁም የጨረታውን ቅጽ የሚሞላው ሰው ስም ከላይ ከተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 የሥራ ቀናት ውስጥ ተወዳዳሪዎች አሸናፊነታቸው ከተገለጸ ጀምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የክፍያ ትዕዛዝ የሚሰጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም (ሲፒኦ) የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስገባትና ውል መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህንን ካላደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ብር ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ዩኒዬኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በዩኒየኑ ግዥና ሽያጭ መመሪያ መሠረት የሚሰተናገድ ይሆናል፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 10 32 /640 /09 00 31 89 07 በመደወል በመጠየቅ መረዳት ይችላል፡፡
- ማሳሰቢያ፡- የመክፈቻ ቀን ካላንደር ወይም እሁድ ቀን ከሆነ በቀጣይ ቀንና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
የዳሞት ሁለ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒዬን ኃ.የተ