Be'kur (Sep 14, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በደቡብ ጎንደር ዞን የአንዳቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ለ2019 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1. የፅዳት እቃዎች፣ ሎት2. የፅህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት3. የኤሌክትሪክ እቃ፣ ሎት4. የዉሃ እቃ፣ ሎት5. የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ ሎት6. ህትመት፣ ሎት7. የጭነት አገልገሎት ሎት8. የቢሮ እቃዎች፣ ሎት9. የላብራቶሪ የሲቢሲ ሬጀንት እቃዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
1. የመታደሻ ወቅቱ ያላለፈበት ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ ቲን ያላቸው፡፡
3. የግዥ መጠኑ 500‚000 (አምሰት መቶ ሽ) ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
4. ተጫራች ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
5. የሚገዙ እቃዎች አይነትና ዝርዝር መገለጫ በጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
6. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶሰት መቶ) በመክፈል ቢሮ ቁጥር 25 ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ እና ከተፈቀደላቸዉ የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ እንደተጫራቹ ምርጫ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት) ለእያንዳንዱ ሎት የጠቅላላ ግዥዉን ብር 8‚000 (ሰምንት ሽ) ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
8. አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈውን እቃ ዋጋ 10 በመቶ በመክፈል ውል መያዝ አለበት፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወጥ በታሸገ ፓስታ በአ/የመ/ደ/ሆ በግ/ፋ/ን አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 25 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. መ/ቤቱ ካሸናፊ ድርጅቱ ያሸነፋቸውን እቃዎች 20 በመቶ ከውል በፊት የመጨመርም ሆነ የመቀነሰ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
11. ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ነው፡፡
12. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም በግ/ፋ/ን አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 25 ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን 11፡30 ይታሸጋል በ11ኛው ቀን 3፡00 ላይ ይከፈታል፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. ከጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
15. ጨረታውን የሚከፈትበት ቀን የበአል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል፡፡
16. ውል መያዝ የሚቻለው የጨረታው አሸናፊ ተጫራቹ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5የሰራ ቀናት በኋላ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውሰጥ ውል መያዝ አለበት፡፡
17. ውድድሩ የሚካሄደው በእያንዳንዱ ሎት ጠቅላላ ዋጋ ነው ፡፡
የአንዳቤት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል