Addis Zemen (Sep 15, 2026)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በጀት አመት የአንድኛ (1ኛ)ዙር ጨረታ፡
- በሎት1፡- የፅዳት ዕቃዎች ግዥ
- በሎት 2፡- የደንብ ልብስ በሎት ግዥ
- በሎት1፡- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ
- በሎት 4፡- የደንብ ልብስ በሎት 4 ግዥ
- በሎት 5፡- የመኪና እቃዎች ግዥ
- በሎት 6፡- የኤሌክትሮኒክስ (የአይቲ) እቃዎች ግዥ
በሎት 6 በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በተጨማሪም በአገልግሎት ሥራዎች ፦
- በሎት 1፦- የመስተንግዶ ስራዎች፣
- በሎት 2፡- የህትመት ስራዎች
- በሎት 3፦ የኤሌክትሮኒክስ (የአይቲ) እቃዎች ጥገና ስራዎች
- በሎት 4፡- የኤሌክትሮኒክስ (የአይቲ) እቃዎች መለዋወጫ አቅርቦት
- በሎት 5 የልብስ ስፌት ስራዎች
- በሎት 6፡- የቢሮ ቋሚ ዕቃዎች ጥገና ስራዎች
- በሎት 7 የዲኮር ስራዎችን
- በሎት 8፡- የትራንስፖርት አገልግሎት ስራዎች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ሎቶች መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች በአቅራቢ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆኑን እና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የታደሰ የንግድ ፈቃድና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
- የጨረታ ሰነዱ የመወዳደሪያ ዋጋ በሙሉ ታሽጎ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማሰገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት ሁሉ ናሙና ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች በአንድ እቃ አይነት ሁለት ናሙና ማቅረብ የለባቸውም::
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት ሁሉ ናሙና ላይ ድርጅታቸውን የሚገልፅ ማንኛዉም ምልክት (ማህተም) ማስቀመጥ የለባቸዉም::
- ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር በየሎቱ 300 /መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የሚታሸግ ሲሆን 4፡30 ሳጥኑ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የመወዳደሪያ ዋጋ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ወስጥ ማስገባት የምትችሉ ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይሆናል።
- ተጫራቾች ዋጋቸውን በወሰዱት የጨረታ ሰድ ይ ብቻ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች በወሰዱት ሰነድ ላይ በእስኪርብቶ እስፔክ ማስተካከል አይችሉም።
- የጨረታ ዋስትና በየሎቱ 2% ሲፒኦ ብቻ ሲሆን የምንቀበለው ቼክ አንቀበልም በተጨማሪ ተጫራቾች አሸናፊ ሆነው ሲቀርብ አሸናፊ የሆነበትን 10% ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የዋጋ የጊዜ ገደብ ማስቀመጥ አይችሉም::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፦ ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ ወይም መረጃ ለማግኘት ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር 01111266384 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ ፡- ፒያሳ ገዳም ሰፈር ከጊዮርጊስ ጀርባ ወደ ዳክስን መሄጃ ወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት 2ኛ ፎቅ::
የአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት