በላይነህ ክንዴ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወደ ተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክት ሳይቶች የኮንስትራክሽን ግብዓቶች (ጭነት) የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በላይነህ ክንዴ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወደ ተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክት ሳይቶች የኮንስትራክሽን ግብዓቶች (ጭነት) የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል


Reporter (Sep 20, 2026)

የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን በላይነህ ክንዴ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ወደ ተለያዩ የግንባታ ፕሮጀክት ሳይቶች የኮንስትራክሽን ግብዓቶች (ጭነት) የሚያጓጉዙ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የትራንስፖርት አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል:: በመሆኑም ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና በቂ ተሽከርካሪዎችን ማቅረብ የሚችሉ ትራንስፖርተሮች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፦

በዚህም መሠረት፡

  1. ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ግዥ ክፍል መውሰድ ይቻላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስረከቢያ ዋጋቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ማስታወቂያው መውጫ ቀን ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
  4. የሚያቀርቡት ዋጋ 10 ፐርሰንት ጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) በጥሬ ገንዘብ፤ በቼክ ወይም ባንክ በተመሰከረለት ..ኦ፤ ለብቻ በአነስተኛ ፖስታ በሰም የታሸገ ዋጋ ማቅረቢያ ወይም ፕሮፎርማ ኢንቮይስ ማቅረብ አለባቸው፤
  5.  ከላይ የተጠቀሱት ማስረጃዎች እና ሌሎችም ተወዳዳሪዎች ለውድድር ይጠቅመኛል የሚሏቸው ማስረጃዎች መቅረብ ይችላሉ።

ከላይ የተጠቀሱት ሁሉም ማስረጃዎች በትልቅ ፖስታ ውስጥ በሰም ታሽገው እና ማህተም አርፎባቸው መቅረብ እና አራት ኪሎ፤ አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ህንጻ የምድር ወለል በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ እስከ መስከረም 20 ቀን 2019 . ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን አስመዝግበው እስከ ቀኑ 800 ሰዓት ማስገባት አለባቸው።

የጨረታ ሳጥኑ መስከረም 20 ቀን 2019 . ከቀኑ 800 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 830 ሰዓት ተጫራጮች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

አሸናፊዎች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ድርጅቱ ከአሳወቀ ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ  ውል መያዝ አለባቸው:: በተጠቀሰው ጊዜ ውል ካልያዙ የጨረታ ማስከበሪያው ገንዘብ ተመላሽ አይሆንም::ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ድርጅቱ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *