የኮካ-ኮላ ምርቶችን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች አከፋፋይ መሆን ለሚፈልጉ የቀረበ ጥሪ – test3.diretenders.com

የኮካ-ኮላ ምርቶችን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች አከፋፋይ መሆን ለሚፈልጉ የቀረበ ጥሪ


Reporter (Sep 20, 2026)

የኮካ-ኮላ ምርቶችን በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች አከፋፋይ መሆን ለሚፈልጉ የቀረበ ጥሪ

ኮካኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ፣ ሐዋሳ፣ አዳማ፣ ወራቢ፣ ቡታጅራ፣ በባቆ እና በዙሪያው ባሉ ከተሞች፣ በደሴ፣ መቀሌ፣ ሐረር፣ ጂንካ፣ ሂርና፣ ጨለንቆ፣ ቆቦ፣ ደልጊ፣ ማይፀብሪ፣ ላሊበላ፣ ኮምቦልቻ (ሐረርጌ)፣ ፊቅ (ሶማሌ ክልል)፣ ቦንጋ፣ ድሬዳዋ እና ወላይታ የኮካ ኮላ ምርቶችን በማከፋፈል የንግድ አጋሮቻችን መሆን የሚችሉ አስተማማኝ እና የካፒታልም ሆነ ሙያዊ ብቃት ያላቸው የሀገር ውስጥ አከፋፋዮችን በመፈለግ ላይ ይገኛል። ይኸውም በወራቤ እና በቡታጅራ ለሚገኙ ብቁ ለሆኑ አከፋፋዮችን የአጋርነት ጥሪያችንን እናቀርባለን።

መሰረታዊ የተሳትፎ መስፈርቶች

ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የሚከተሉትን መሰረታዊ መስፈርቶች ማሟላት ከቻሱ እንዲሳተፉ እንጋብዛለን፣

  • ስራው የሚጠይቀውን የስራ ማስኬጃ ካፒታል፡ በኢትዮጵያ ብር ማቅረብ የሚችል
  • በትንሹ 350 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መጋዘን ያለው እና የመጠጥ ምርቶችን ለማከማቸት እና ለማከፋፈል ተስማሚ የሆነ ጥሩ መሰረተ ልማት ያሉት
  • በገበያ ላይ ምርቶችን በስፋት ለማሰራጨት የሚያገለግሉ እንደ የጭነት መኪና፤ ፒክአፕ እና በእጅ የሚገፉ ጋሪዎችን ማቅረብ የሚችል
  • የለስላሳ መጠጦችን እና በፍጥነት በዝቅተኛ ዋጋ ወደተጠቃሚ የሚደርሱ ምርቶችን በማሰራጨት ረገድ የተረጋገጠ ልምድ ያለው በመጨረሻም
  • የኮካ-ኮላን የጥራት እና የአገልግሎት አሰጣጥ መስፈርቶችን በሚገባ አሟልቶ ከድርጅታችን ለመግዛት እና ለማከፋፈል ፈቃደኛ የሆነ እና አቅሙ ያለው

የቴክኒክ እና የፋይናንስ ብቃቶች

ፍላጎቱ ያላቸው ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርባቸዋል፦

  • የለስላሳ መጠጦችን እና በፍጥነት በዝቅተኛ ዋጋ ወደተጠቃሚ የሚደርሱ ምርቶችን በማሰራጨት ረገድ የተረጋገጠ ልምድ ያለው እና ማሳየት የሚችል
  • በገበያው ላይ የሚኖረውን ትልቅ የምርት ፍላጎት መሸፈን የሚችል የተደራጀ የሎጂስቲክስ እና መሠረተ ልማት ያለው
  • ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና በኢትዮጵያ ውስጥ መጠጦችን ለማከፋፈል የሚያስፈልጉትን ህጋዊ ቅድመ ሁኔታዎች ያሟላ እና ማቅረብ የሚችል
  • የማከፋፈያ ሥራው ከመጀመሪያው ከሚጠበቀው በላይ ቢያድግ ካለው ሀብት ወይም ከፋይናንስ ተቋማት ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ የማግኘት አቅም ያለው

የዲጂታል እና የቴክኖሎጂ ቅድመ ሁኔታዎች፡

  • የIT መሰረተ ልማት እና የኢንተርኔት ግንኙነት ያለው
  • ኮምፒውተር እና ስማርት ስልኮች
  • የኮካ-ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ በኢትዮጵያ (ሲሲቢኤ በኢትዮጵያ) ሶፍትዌር ሲስተሞችን በተለይም ለሽያጭ ክትትል እና ኢንቬንቶሪ (ስቶክ) አስተዳደር የሚያገለግሉትን ለመጠቀም ዝግጁ የሆነ

የጨረታ ማቅረቢያ መመሪያዎች፡

ብቁ እና ፍላጎት ያላቸው የንግድ ድርጅቶች የሚከተሉትን የሚያጠቃልሉ ሙሱ ፕሮፖዛሎችን እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል፡

  • ስለድርጅቱ እና ከዚህ ቀደም በዘርፉ ያለውን ልምድ በግልጽ የሚያሳይ ዝርዝር መገለጫ/ፕሮፋይል/
  • ንግዱን ለመጀመር የሚያስችለውን የካፒታል መጠን እና የገንዘብ ድጋፍ እንዳለው የሚያረጋግጡ ትክክለኛ ሰነዶች
  • ሊያቀርቡት ስለሚችሉት የመጋዘን እና የመጓጓዣ መሠረተ ልማት ዝርዝር መረጃ
  • 2በኢትዮጵያ ውስጥ አከፋፋይ ሆነው ለመስራት ህጋዊ ፈቃድ ማግኘትዎን የሚያረጋግጡ ትክክለኛ የንግድ ፈቃዶች እና ሌሎች ኦፊሴላዊ ሰነዶች

የፕሮፖዛል ማስረከቢያ የመጨረሻ ቀን፡ መስከረም 07 2019 ዓ/ም

ፕሮፖዛል ማስገቢያ ኢሜይል አድራሻ፡ salemu2@ccbagroup.com

ኮካ-ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ በኢትዮጵያ (ሲሲቢኤ በኢትዮጵያ)

አድራሻ፡ ኮካ-ኮላ ማዞሪያ፤ ጅማ መውጫ መንገድ ላይ

ፖ.ሳ.ቁ 1346

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ኮካ-ኮላ ቤቨሬጅስ አፍሪካ በኢትዮጵያ ታማኝ እና ብቁ ከሆኑ የስራ አጋሮች ጋር ጠንካራ እና ውጤታማ አጋርነት ለመፍጠር ቁርጠኛ ሲሆን ይህም በኢትዮጵያ በሁሉም ስፍራዎች ተፈላጊ የሆነው የኮካ-ኮላ ምርታችን ለደንበኞቻችን እንዲሁም ተጠቃሚዎቻችን በሚፈልጉት መጠን እንዲደርስ የሚያስችል ቀልጣፋ አሰራርን ለማረጋገጥ ያለመ ነው።

East Africa Bottling S.C.

Company Registration No.

MT/AA/3/2004

Jimma Road

P.O.Box 1346 

Addis Ababa, Ethiopia

+251(0)112 75 61 14

T +251(0)112 76 51 03— 08

F +251(0)112 75 31 52


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *