በን/ፋ/ስ/ላ/ክ/ከተማ የላፍቶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለመማር ማስተማር የሚያስፈልጉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በን/ፋ/ስ/ላ/ክ/ከተማ የላፍቶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለመማር ማስተማር የሚያስፈልጉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 22, 2026)

የመጀመሪያ ዙር ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በን/ፋ/ስ/ላ/ክ/ ከተማ የላፍቶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት

  • በሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፤
  • በሎት 2 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣
  • በሎት 3 አላቂ የጽዳት ዕቃዎች፣
  • በሎት4 የደንብ አልባሳት እና የስፖርት መምህራን ልብስ፤
  • በሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፤
  •  በሎት6 ቋሚ ዕቃዎች፣
  • በሎት 7 የህክምና ዕቃዎች፣
  • በሎት 8 የጥገና ዕቃዎች
  •  በሎት 9 ለመማር ማስተማር የሚያስፈልጉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፤

በዚህም መሰረት፡-

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር / TIN number/ ያላቸው ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ /AT/ የተመዘገቡና ለመመዝገባቸውም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  2. የተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ ከመ/ቤቱ በወሰዱት የጨረታ ዋጋ ከመ/ቤቱ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ብቻ ስርዝ ድልዝ ይኖረው በጉልህ በሚታይ መልኩ ከቫት በፊትና ከባት በኋላ ያለውን ዋጋ ፅፈው የድርጅቱ ተወካይ ስምና ፊርማ እንዲሁም የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርገው በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  3.  ተጫራቾች ለወሰዱትና ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት በሚሞሉት አጠቃላይ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ2% የጨረታ ማሰከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ናሙና እንዲገባ በተጠየቀባቸው የእቃ አይነቶች ሁሉ ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው::
  5. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት አንድ ሎት ብር 300.00/ ብር ሶስት መቶ/ በመክፈል ከመ/ቤቱ ረ/ፋ/ኦፌሰር ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት መግዛትና መውሰድ ይኖርባቸዋል።
  6. በጥቃቅንና አንስተኛ የተደራጁ ተቋማት ራሳቸውን አምርተው ለገበያ ከሚያቀርቡት  ወይም ተጨማሪ እሴት ጨምረው ከሚያቀርቡት እቃ ወይም ምርት ውጪ የተዘጋጀ ዕቃዎችን ገዝተው በሚወዳደሩበት ጊዜ እንደማንኛውም ተጫራች ድርጅት የጨረታ ስነድ መግዛት፤ የጨረታና የውል ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል::
  7. ተጫራቾች አሸናፊ ሆነው ለተገኙባቸው እቃዎች የሞሉትን አጠቃላይ ዋጋ በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO በማስያዝ ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ላሸነፉበት እቃዎች መ/ቤቱ ምንም አይነት የዋጋ ለወጥ ሳያደርግ ብዛቱን 20% ዝቅም ከፍም አድርጎ ሊያስተካክል ይችላል።
  9. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ ሰነድ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግና በኤንቨሎፕ በማሸግ ማስታወቂያ ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ የ10 የስራ ቀናት ት/ቤቱ በአዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 3 በመገኘት በሰዓቱ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
  10. የጨረታ ሰነዱን የመመለሻ ቀንና ስዓት ካለፈ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድና በጨረታመክፈቻ ላይ ያልተነበበ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  11. የጨረታው ሳጥን ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በአስረኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እና/ወይም ባይገኙም የሚከፈት ይሆናል።
  12. ውል የተዋዋሉ አሸናፊዎች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት የግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ንብረት ማከማቻ ክፍል ውስጥ ማምጣትና ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ ሙሉ መብት የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ላፍቶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስልክ ፡- 011 -4 71-06 45 /011-4 71 06 42

በን/ፋ/ስ/ላ/ክ/ ከተማ  የላፍቶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት