በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 21, 2026)

በጉምሩክ ኮሚሽን . ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት የተያዙና የተወረሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 11/2019

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ //ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ

የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ከፍሎች፣

  • የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣
  • የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣
  • የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣
  • የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች
  • የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2019 . ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑን እንገልጻለን።

በመሆኑም

1. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ ዕሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

2. በጨረታው ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።

3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሐሙስ መስከረም 14 ቀን 2019 . ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅጽ/ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

4. በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ//ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

.

የቅ//ቤቱ ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

አ.አ.ቃሊቲ ጉምሩከ //ቤት

የእቃ ግልፅ

እስከ 19/01/2019

20/01/2019 345 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 400 ሠዓት ይከፈታል።

6. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡ኢአ ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

7. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ 3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።

9. ከላይ በተ/ 8 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

10./ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩክ፡– 011 ~ 470 – 85 03

አድራሻ፡ሳሪስ አቦ / በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መገንጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

የአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት