Addis Zemen (Sep 22, 2026)
የኮምፒውተር ወረቀትና አላቂ የቢሮ እቃዎች የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ኢ/ኤ/አገ/ደብ/ሪ/ግ/001/2019
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ብርሃን ሪጅን ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት |
የቢሮ መገልገያ እቃዎች |
የጨረታ ዋስትና |
የሚዘጋበት ቀን |
የሚከፈትበት ቀን |
|
ሎት 1 |
የኮምፒውተር ወረቀትና አላቂ የቢሮ እቃዎች |
100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ
|
መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት |
መስከረም 22 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት |
|
ሎት 2 |
የፕሪንተር ቀለሞች፤ የሞተር ሳይክል ጎማ፤ የተሽከርካሪ ባትሪ፤ የባጃጅ ጎማ እና የባጃጅ ባትሪ |
70,000.00 (ሰባ ሺህ ብር ብቻ)
|
መስከረም 22 ቀን 2019 ጠዋት 4፡00 |
መስከረም 22 ቀን 2019 ጠዋት 4፡30
|
|
ሎት 3 |
የተለያዩ ዓይነት የቢሮ መጠቀሚያ ማሽኖች (ኮምፒውተር፣ፕሪንተር፣ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ…) |
200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር ብቻ) |
መስከረም 22 ቀን 209 ከቀኑ 10፡30 |
መስከረም 22 ቀን 2019 ከቀኑ 10፡30 |
1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫራቾች የመንግስት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ደብረ ብርሃን ሪጅን አፄ-ዝርዓያቆብ ህንፃ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ብርሃን ሪጅን ሰፕላይ ቼይን ማኔጂመንት ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 306 የማይመለስ ብር 500.00(አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /cp0/ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መስከረም 22/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ሰፕላይ ቼይን ማኔጂመንት ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 306 የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ቼከ/CPO} ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ቴክኒካል «ኦሪጅናል እና ኮፒ» እና ፋይናንሻል «ኦሪጅናል እና ኮፒ» በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አዝደብሪ ግጨ/001/2019 የሚል ምልክት በማድረግ እስከ መስከረም 22/209 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 306 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ጨረታው ከላይ በተጠቀሱት ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል።
8. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-637-60-94 መደወል ይችላሉ።
9 ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደብረ ብርሃን ሪጅን ጽ/ቤት