Addis Zemen (Sep 21, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 (ሀ – ሠ) በተዘረዘረው መሠረት በሐረሪ ከተማ ለቅይጥ ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውሉ የተዘጋጁ ይዞታዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡
የቦታዎቹ ዝርዝር መግለጫ፦
1. ሐመሬሳ ኢንዱስትሪ ዞን 2. ኤስ ኦ ኤስ አካባቢ 3. ሪፍቲ ቫሊ አካባቢ 4. ገስት ሀውስ አካባቢ 5. ቀላዳንባ ኮንዶሚኒያም አካባቢ 6. ደከር የቀድሞ ኬላ አካባቢ የተጫራቾች መመሪያ እና የመወዳደሪያ መስፈርቶች፦
- የሰነድ ሽያጭ፦ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተወዳዳሪ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የቦታውን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) በመከፈል በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር (3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32) ዘወትር በሥራ ቀናትና በሥራ ሰዓት መግዛት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- የሰነድ ማስገቢያ ጊዜ፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ሰነዱን በመግዛት ለቦታዎች በካሬ ሜትር የሚያቀርቡትን ዋጋ እና የሚከፍሉትን የሊዝ ቅድመ ክፍያ በጨረታ መወዳደሪያ መልስ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የሳጥን መዘጋትና መክፈቻ፦ የጨረታ ሳጥኑ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ተዘግቶ፣ በዚያኑ ዕለት መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ የሚከፈት ይሆናል።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO)፦ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ቦታ የጠቅላላው የቦታ ስፋት በመነሻ ዋጋው ተባዝቶ ከሚገኘው ውጤት 5% (አምስት በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ በጥቅሉ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የቅድመ ክፍያ መጠን (Minimum Down Payment) ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሊዝ ቅድመ ክፍያ መጠን ከአጠቃላይ የሊዝ ዋጋ ከ 30% (ሰላሰ ፐርሰንት) ማነስ የለበትም።
- የግምገማ ነጥብ አሰጣጥ፦ የተጫራቾች አሸናፊነት የሚለየው ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሊዝ ዋጋ 80% (ሰማንያ ፐርሰንት) እና የቅድመ ክፍያ መጠን 20% (ሃያ ፐርሰንት) ጥምር ውጤት ተሰልፎ በሚገኘው ከፍተኛ ነጥብ መሠረት ይሆናል።
- የCPO ተመላሽ፦ የጨረታው አሸናፊዎች ተለይተው በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በይፋ ከተገለጹ በኋላ በጨረታው ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ በባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ይፋዊ ድረ–ገፅ https://hudco.gov.et/ በመግባት ወይም በአካል ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል።
ማሳሰቢያ፡– ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ባለሥልጣን