Addis Zemen (Sep 22, 2026)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ከተማና መሠረተ ልማት በ2019 በጀት ዓመት ከውስጥ ገቢ ከማዘጋጃ ቤት ጀርባ አንስቶ እስከ እስታዲየም መግቢያ ድረስ የኮብል እስቶን እና ዲች ቦይ ግንባታ ሥራ በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፡-
1 ደረጃቸውGC/RC 5 የሆኑ ተጫራቾች በ2018 ዓ.ም የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ (ክሊራንስ ያላቸው) በክልል ወይም በፈዴራል በክልሉ ንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ወይም መምሪያ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ህጋዊ ብቃት ያላቸው እና ማረጋገጫና ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ / BID Security 65,000 /ስልሳ አምስት ሺህ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO ወይም Unconditional bank guarantee ማቅረብ ይኖርበታል።
2. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ አና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸውሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።
3 በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በይርጋለም ከተማ በፒሮጀክቱም ሆነ በመደበኛ በጀት ሥራ ውል ስምምነት ገብተው ሥራ ጀምረው ያላጠናቀቁ (ያልጨረሱ) ተቋራጮች 10. ጨረታውን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
4. በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፈቃዳቸውን ተ.እ.ታ (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ20 (ሀያ ) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት ብር በመክፈል ደረሰኛቸውን በመያዝ ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ/ፋይናንስ ክፍል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾቹ ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።
6. የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/security)፣ ፋይና አባል አንድ ኦርጅናል እና ሀለት ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 2:30 እስከ 5:30 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥ ፋይናንስ ክፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።
7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 5፡30 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
8. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል።
10. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
11. በጨረታ አከፋፈት ሥነ -ሥርዓት ላይ የተነበበው ዋጋ አርቴሜቲክ ቼክ በሚደረግበት ጊዜ በሁለቱም መካከል ያለው ከ2% በላይ በታች ከሆነ ቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል።
12. የቀረበው ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒው የማይታይ እና የማይነበብ ከሆነ እንዲሁም የሚያጠራጥር ሁኔታ ቢገኝ ኦርጅናሉን የማቅረብ ግዴታ አለበት።
13. በጨረታ ላይ ያለው ጠቅላላ ዋጋ ከመሐንዲስ ግምት /ከወቅቱ ከገበያ ዋጋ 15% በላይ ከሆነ እና ከ 30% በታች ከቀረበ የወቅቱ የገበያ መዋዠቅ እና የሥራውን አንገብጋቢነት በማስቀደም ከውድድር ውጪ ይደረጋል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት