Addis Zemen (Sep 21, 2026)
የግዥ ጨረታ ማስታወቄያ
የብርሃን ጉዞ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ለትምህርት የሚውሉ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች አላቂ የጽዳት ዕቃዎች የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ፈርኒቸር፣የደንብ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ የላብራቶሪ (ቤተሙከራ ዕቃዎች) የሕንፃ መሣሪያዎች፣ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- የተጠቀሰውን የሥራ ዘርፍ ሕጋዊ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውንና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሚቀርበው አጠቃላይ ዋጋ ጋር 3000.00 ማቅረብ የሚችሉ፤
- አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በተገለፀበት በ5 ቀን ውስጥ ውል መፈፀም እና 10% የውል ማስረከቢያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል ሲሆን የተወዳደረባቸውንም ዕቃ ዋጋ ከነቫቱ ጠቅላላ ድምሩን ሞልቶ ማስገባት አለበት፤
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፤
ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአሥር የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ በት/ቤቱ የፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 4 የማይመለስ 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መወዳደር ይችላሉ። ተጫራቾች በተመረጠው ናሙና መሠረት በ7 ቀን ውስጥ ዕቃዎችን በመ/ቤቱ ዕቃ ግምጃ ቤት ድረስ ማስረከብ ይኖርበታል።
ተጫራቾች ሠነድ ላይ የተጠቀሱትን ዕቃዎች የሚሸጥበትን ዋጋ እና ከነቫት ሌሎች መረጃዎችን በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው በ25/1/2019 ዓ.ም እስከ 4፡00 ሰዓት ለዚህ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
ጨረታው የሚከፈተው በማግስቱ በ26/1/2019 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
መ/ቤቱ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብት አለው።
አድራሻ
ካዛንችስ እንደራሴ ሆቴል ከፍ ብሎ ብርሃን ጉዞ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለበለጠ መረጃ፡- 011-557-85-40/011-557-85-38 (0115547365)
የብርሃን ጉዞ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት