ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም. ለመማር ማስተማር ሂደት የሚያገለግሉ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም. ለመማር ማስተማር ሂደት የሚያገለግሉ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 22, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም ለመማር ማስተማር ሂደት የሚያገለግሉ፣ የአውቶሞቲቭ እቃዎች ኤሌትሪክ እና ኤሌክትሮኒክስ ማኑፋክቸሪንግ የአይሲቲ ዕቃዎችን፤ ሰርቬይንግ እና ድራፍቲንግ እቃዎች የሆቴል እና ቱሪዝም እቃዎች፤ ውድዎርክ የአይሲቲ እቃዎች፤ ቴክስታይል እና ጋርመንት እቃዎችን፤ የኮንስትራክሽን እቃዎች፣ የጽህፈት እቃዎች፤ የጽዳት እቃዎች፣ የጤና እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሁሉ ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

1.ተጫራቾች የቫት ተመዝጋቢ፣ በስራው መስክ ህጋዊና የታደሠ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉና የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣

2.ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለዕያንዳዱ ሰነድ 5000.00 (አምስት ሺ ብር) በባንክ በተመሠከረ ቼክ (CPO) ከጨረታ ሠነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ የግዢ እና ፋይናንስ ንብረት ዳሬክቶሬት ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡

4.በጨረታው አሸናፊ የሚሆኑ ተጯራቾች በጨረታ ሠነድ ላይ ለተዘረዘሩት ዕቃዎች (ለተጫረቱበት) አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከእያንዳንዱ ዕቃና ሙና ወይም Sample ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች ላሸነፉባቸው ዕቃዎች የጠቅላላ ዋጋ 10% በውል ማስከበሪያነት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በገዙት የጨረታ ሠነድ ላይ ባለው ዝርዝር ሞልተው ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው በኮሌጁ የጨረታ ሳጥን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት ማስገባት ይችላሉ፡፡

7. የጨረታው ሳጥን የሚዘጋው በ16ኛ ቀን በዕለቱ በ 3፡30 ሠዓት ሆኖ ጨረታው የሚከፈተው በተመሳሳይ ቀን 4፡00 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ የግዢ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡

8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በ10 ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ ኮሌጁ ግቢ ድረስ አምጥተው ያስረክባሉ፡፡

9. ተጫራቾች በገዙት የጨረታ ሰነድ ዋጋ ሲሞሉ አጠቃላይ ድምር መቀመጥ ይኖርበታል፡፡

10. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብትአለው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0251113266 ወይም 02511117602 በመደወል ማብራሪያመጠየቅ ይችላሉ፡፡

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ