Melekite Dire (Sep 23, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
በድሬደዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ፑል በስሩ ለሚገኘው ለጽዳትና ውበት ለ2019 በጀት አመት ለስራ የሚያገለግሉ የጽዳት ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ጨረታውን መወዳደር ለምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ መስፈርት፡–
- በዘርፉ የተሰማራ የንግድ ፈቃድ ያለው
- የዘመኑን ግብር የከፈለ
- የግብር ከፋይነተ መለያ ቁጥር (Tin No) ያለው
- የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
- በመ/ቤቶች መልካም አፈፃጸም ያለው
- የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ) በ CPO በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
- መ/ቤቱ ባዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ላይ በአቅራቢነት መሞላት ያለበት እያንዳንዱ የሰነድ ክፍል ተሞልቶ የተጫራቾች ፊርማና ማህተም ከሌለው ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነድ የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል የፑሉ ፋይናስ ክፍል መግዛት ትችላላችሁ
- ጨረታው በድሬ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 21 ቀን አየር ላይ ውሎ በ22 ተኛ ቀኑ ይከፈታል በዚያው ቀን 3፡30 ሰዓት ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል።
- የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባችሁ
ማሳሰቢያ መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ በስ/ቁ 0915755324
አድራሻ፡– የድሬደዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ቢሮ (ቴሌ ትራፊክ መብራት አጠገብ