የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍርድ አፈጻጸም ከሳሽ ለታ ጣፋ እና ተከሳሾች ዱሬቲ ኃ.የተ.የግ.ማ. እና ሞኮንንን አብዲሳ መካከል ባለው የፍትሐ ብሔር ክርክር መጋዘን/ንብረት በሐራጅ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍርድ አፈጻጸም ከሳሽ ለታ ጣፋ እና ተከሳሾች ዱሬቲ ኃ.የተ.የግ.ማ. እና ሞኮንንን አብዲሳ መካከል ባለው የፍትሐ ብሔር ክርክር መጋዘን/ንብረት በሐራጅ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 25, 2026)

ማስታወቂያ

በፍርድ አፈጻጸም ከሳሽ ለታ ጣፋ እና በፍርድ አፈጻጸም ተከሳሾች ዱሬቲ ኃ.የተ. የግ.ማ. እና ሞኮንንን አብዲሳ መካከል ያለውን የፍትሐ ብሔር አፈጻጸም ክርክር በተመለከተ፤ በይዞታ ካርታ ቁጥር BMG/K/L/TA/2014 የሚታወቀው እና GMZ የተባለው መጋዘን ወይም ንብረት ይህ ፍርድ ቤት በሐራጅ መሸጥ ስለሚፈልግ፤ የመነሻ ጨረታ ዋጋው 68,348,385 (ስልሳ ስምንት ሚሊዮን ሦስት መቶ አርባ ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ሰማንያ አምስት ብር) ሆኖ ከቀን 15/01/2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ቀን 15/02/2019 ዓ.ም. ድረስ በአየር ላይ ቆይቶ፣ በቀን 16/02/2019 ዓ.ም. ጠዋት ከ3፡00 እስከ 6፡30 ሰዓት በተገኘው ከፍተኛ ዋጋ የሚሸጥ ስለሆነ፣ መግዛት የሚፈልጉ አካላት የመነሻ ጨረታውን 1/4 CPO በማስያዝ ተወዳድረው እንዲገዙ ውጤቱን ለቀን 18/02/2019 ዓ.ም. ቀጠሮ 4፡00 ሰዓት ሪፖርት እንድታደርጉ የሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አዟል።

ማሳሰቢያ እና ተጨማሪ መረጃ

1. ማንኛውም ባለጉዳይ መልስ ወይም የትዕዛዝ ውጤት በሸገር ኢ–ኮርት ወይም በፖርታል እንድትልኩ ከዚህ ውጪ በአካል ይዘው የሚቀርቡትን የማናስተናግድ መሆኑን።

2. በኮምፒውተር የሆነ መልስ የሚጻፍበት ስታይል “Times New Roman” የፎንት መጠን 12 ጽሑፍ መስመር ርቀት 1.5 መሆን አለበት።

3. ከቀጠሮ በፊት ጉዳዩን ለማወቅ በሸገር ኢ–ኮርት በኩል በመግባት ማወቅ ይቻላል እንዲሁም በአጭር ስልክ 8794 ላይ በመደወል ይጠይቁ።

4. ጉዳያችሁን በቪዲዮ ኮንፊረንስ VK ብቻ የምትከታተሉ መሆኑን አውቃችሁ ለእናንተ ቅርብ በሆነው ፍርድ ቤት ተታተሉ።

የሸገር ከተማ–ከፍተኛ ፍርድ ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *