Melekite Dire (Sep 23, 2026)
የአካባቢ ጨረታ ማስታወቂያ
የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ለ2019 በጀት ዓመት የውሃ ማሰራጫ መስመር ለመዘርጋት ሰላስፈለገ TOYOTA DOUBLE CABIN 4WD ሞዴል ኤር ኮንዲሽነር ያለው ተሽከርካሪ በቀን ያለነዳጅ በግልፅ ጨረታ አወዳድረን ለአንድ አመት ውል ፈፅመን ለመከራየት እንፈልጋለን፡፡ እንዲሁም እንደሰራው ሁኔታ እየታየ የሚራዘም ይሆናል፡፡
ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና መታወቂያ ያላቸው፡፡
- ቫት የተመዘገበ የ 2018 ዓ.ም መጨረሻ ወር ቫት ዲክለር ያደረገ ቲን ቁጥር ያለው፡፡
- በዘርፉ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማቅረብ የሚችል
- የጨረታው ዶክመንት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ከግዥና ፋይናንስ ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 09 በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላል፡፡
- ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ3፡00 የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በተመሣሣይ ቀን 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ፖስታ የእያንዳንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት በተጨማሪ በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው መቅረብ አለባቸው፡
- ያሸነፈው ተጫራች የተጠየቀውን ተሽከርካሪ የአገልግሎት ግዥ ትዕዛዝ እንደተሰጠው በድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ስራዎችን በሚያከናውንባቸው አስከ 12 ኪሎ ሜትር ድረስ የሚሰራ ይሆናል፡፡
- በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
- ጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ዶክመንት ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቀበሌ 03
ድሬዳዋ
ስልክ ቁጥር 025 112 4892
ፖሣ.ቁ 446