የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን በ2018/19 በጀት ዓመት ፕሪንተሮች፣ የፎቶኮፒ፣ የፋክስ እና ሌሎች ተመሳሳይ የቢሮ ዕቃዎችን በዋናው ቢሮና ቅ/አገልግሎት መስጫ በመምጣት ሰርቪስ ማድረግና መጠገን ስራ የአገልግሎት ግዢ በአካባቢ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት ውል ፈጽሞ ለማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን በ2018/19 በጀት ዓመት ፕሪንተሮች፣ የፎቶኮፒ፣ የፋክስ እና ሌሎች ተመሳሳይ የቢሮ ዕቃዎችን በዋናው ቢሮና ቅ/አገልግሎት መስጫ በመምጣት ሰርቪስ ማድረግና መጠገን ስራ የአገልግሎት ግዢ በአካባቢ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት ውል ፈጽሞ ለማሰራት ይፈልጋል


Melekite Dire (Sep 23, 2026)

በድጋሚ የወጣ የአካባቢ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን በ2018/19 በጀት ዓመት ፕሪንተሮች፣ የፎቶኮፒ፣ የፋክስ እና ሌሎች ተመሳሳይ የቢሮ ዕቃዎችን በዋናው ቢሮና ቅ/አገልግሎት መስጫ በመምጣት ሰርቪስ ማድረግና መጠገን ሰራ የአገልግሎት ግዢ በአካባቢ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለሁለት ዓመት ውል ፈጽሞ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

እንዲሁም የአገልግሎቱን ጥራት እና ቀልጣፋ አገልግሎት ታይቶ ለተጨማሪ ጊዜ የሚራዘም ይሆናል፡፡

ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡

  • የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና የአቅራቢዎች መታወቂያ ያላቸው፡፡
  • ቫት የተመዘገበ ሆኖ መጨረሻ ወር ቫት ዲክለር ያደረገ እና ቲን ቁጥር ያለው፡፡
  • የጨረታው ዶክመንት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመከፈል ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ከግዥ ፋይናንስና ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 05 በጥሬ ገንዘብ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታ ሰነድ በውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቢሮ ቁጥር 05 ከ1፡30 እስከ 11፡30 ዘወትር በስራ ሰዓትና ቀን መግዛትና ማስገባት ይቻላል፡፡
  • ጨረታው በማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን በ3፡00 የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ በተመሣሣይ ቀን 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  • ተጫራቾች ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ የጨረታ ማስከበሪያ በተረጋገጠ የባንክ ዋስትና CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ዶክመንቱ ሲከፈት ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ፖስታ የእያንዳንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለበት
  • በተጨማሪ በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ የተዘጋጁት ፎርማት ተሞልተውና ተፈርመው መቅረብ አለባቸው፡፡
    ያሸነፈው ተጫራች የተጠየቀውን አገልግሎት ውል ከተፈፀመ በኋላ በተጠየቀ በ24 ሰዓት ውስጥ የአገልግሎቱን ስራ ማከናወን አለበት፡፡
  • በዶከመንቱ ከተሰጠው ስፔስፊኬሽን ወይም ሳምፕል ወጪ የሚደረግ ጥገና ተቀባይነት የለውም፡፡
  • የሚጠገኑ፣የኮፒውተሮች፣ ፕሪንተሮች፣ የፎቶኮፒ፣ የፋክስ እና ሌሎች ተመሳሳይ የቢሮ ዕቃዎችን እንደቀረቡ እንደ አስፈላጊነቱ በአስቸኳይ ሰርቶ ማቅረብ የሚችል፡፡
    በጨረታው ሂደት ጨረታውን ለማዛባት ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ውጭ እንደሚሆንና በመንግሥት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል፡፡
  • የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ዶክመንት ተቀባይነት የለውም፡፡
  • የባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ድሬዳዋ አስተዳደር ውሃና ፍሣሽ ባለሥልጣን ቀበሌ ዐ3 ድሬዳዋ ስልክ ቁጥር 025 112 48 92 ፖሣ.ቁ 446


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *