መሽረቅ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሳብ ማስመርመር ይፈልጋል – test3.diretenders.com

መሽረቅ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሳብ ማስመርመር ይፈልጋል


Addis Zemen (Sep 29, 2026)

የውጭ ሂሳብ ኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ

መሽረቅ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የውጭ ኦዲተሮችን አወዳድሮ የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ሂሳብ ማስመርመር ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት ተጫራቾች

  1. እውቅና ያላቸውና ከዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸው በመስኩ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉና የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበራትን ሂሳብ በመመርመር የሥራ ልምድ ያላቸው መሆን ይኖርበታል።
  2. የማህበሩን ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችሉትን ዋጋ መጠን ሥራውን አጠናቀው የሚያስረክቡበትን የጊዜ ገደብ መጥቀስ ይኖርበታል።
  3. ተወዳዳሪዎች ዋጋ ከማቅረባቸው በፊት የማህበሩን የሂሳብ ሰነድ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ሲኒማ ራስ ሐጂ ለገሰ ሸረፋ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503/504 በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት መመልከት ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ማለትም ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 እና ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጽ/ቤቱ ማቅረብ ይችላሉ።
  5. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ11ኛው ቀን መስከረም 29/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማህበሩ ጽ/ቤት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡–

ማህበሩ ለሥራው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡– አ/ከ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ሲኒማ ራስ ሐጂ ለገሠ ሸረፋ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 503/504

ስልክ ቁጥር 011 827 7637/ 09 25 59 89 14/ 09 25 69 65 93/ 09 80 63 08 98

መሽረቅ የገበያ ማዕከል አክሲዮን ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *