Addis Zemen (Sep 29, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
ለልዩ ልዩ አገልግሎት የሚውል ክፍት ቦታ ፓርቲሽን ለማሠራት የወጣ ጨረታ
መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር መርካቶ ላይ ባሠራው የገበያ ማዕከል ውስጥ ለልዩ ልዩ አገልግሎት (ለሱቅ፣ ለቢሮ መሰል አገልግሎት የሚውል ክፍት ቦታን በአሉሚኒየም እና በላሜራ የማከፋፈል ሥራ ዕቃውን አክሲዮን ማኅበሩ አቅርቦ ማሠራት ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት፡-
1. ተጫራቾች በመስኩ የንግድና የሙያ ፈቃድ ያላቸው
2. ሥራውን ለመሥራት የሚጠይቁትን የጉልበት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ መቅረብ አለበት
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን ዋናውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 7 የሥራ ቀናት አክሲዮን ማኅበሩ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር433 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት 8ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 011 231 3147/ 011 231 3237 ወይም በአካል ሲዳሞ ተራ መተሳሰብ የገበያ ማዕከል መጠየቅ ይችላሉ።
መተሳሰብ ለእድገት ጠቅላላ ንግድ አክሲዮን ማኅበር