ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.ግ.ማህበር (ኖክ) ቃሊቲ መጋዘን ውስጥ ያሉትን ባለ 1ኛ ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ ፓሌቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.ግ.ማህበር (ኖክ) ቃሊቲ መጋዘን ውስጥ ያሉትን ባለ 1ኛ ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ ፓሌቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


2merkato.com (Sep 29, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን ቃሊቲ መጋዘን ውስጥ ያሉትን ባለ 1ኛ ደረጃ እና 2ኛ ደረጃ ፓሌቶችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ የእቃው ዝርዝር እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

ተ.ቁ

የፓሌት ዓይነት

ብዛት

1

1ኛ ደረጃ ፓሌት

2000

2

2ኛ ደረጃ ፓሌት

300

ስለሆነም ድርጅታችን ፓሌቶቹን ባሉበት ሁኔታ መሸጥ ይፈልጋል። በተጨማሪም ተጫራቾች ፓሌቶቹን እንደከዚህ ቀደም መምረጥ እንደማይችሉ ከወዲሁ ማሳሰብ ይወዳል። ከላይ ለተጠቀሱት እቃዎች ዋጋ በመስጠት መወዳደር ይቻላል። እቃዎቹን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቅዳሜ እና እሁድን ሳይጨምር ቦታው ላይ በመመልከት የሚገዙበትን ዋጋ ከ15 በመቶ ቫት ጋር በመግለጽ ድርጅቱ ለዚህ ጨረታ ያዘጋጀውን ፎርም በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርበታል። ተጫራች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው ሊሆን ይገባል። እንዲሁም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ቢድ ቦንድ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በማቅረብ መጫረት ይቻላል።

አሸናፊ ተጫራች ማሸነፉ በተገለጸለት በሦስት የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን በአንድ ጊዜ ክፍያ መፈጸም ይኖርበታል። ይህንን ባይፈጽም ለጨረታው ያስያዘውን ገንዘብ በሙሉ የማይመለስ በመሆኑ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡ አሸናፊ እቃውን በሰባት ተከታታይ የስራ ቀናት (ቅዳሜ እና እሁድን ሳይጨምር) ከቃሊቲ መጋዘን ማንሳት አለበት። ይህ ባይሆን የመጋዘን ኪራይ በቀን 3,000.00 ብር ይከፍላል። ሙሉ ክፍያ ሲፈጽም እና ሙሉ በሙሉ እቃዎቹ ከቃሊቲ መጋዘን ሲነሱ ብቻ ሲፒኦው ተመላሽ ይሆናል። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁ. 011-618-7165 ወይም 011-439-0378 መደወል ይቻላል፡፡

አድራሻ፡– ቦሌ ኤርፖርት መንገድ ከፍሬንድሺፕ ህንፃ ፊት ለፊት ያለው የኖክ ዋ/መስሪያ ቤት

ናሽናል ኦይል ኢትዮጵያ ኃ.የተ.ግ.ማህበር (ኖክ)


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *