Addis Zemen (Sep 29, 2026)
ለኦዲት አገልግሎት የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ካፒታል የቁጠባና ብድር ህብረት ሥራ ማህበር (Capital Saving and Credit Cooperative) ህጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት ሲሆን፣ በ ‘Peachtree Accounting’ ሶፍትዌር የተመዘገበውን ከመጋቢት 01/2016 እስከ ሰኔ 30/2018 ያለውን ሂሳብ መረጃ ወደ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች (International Financial Reporting Standards IFRS) በማስቀየር (convert በማስደረግ) በውጭ ኦዲተሮች አወዳድሮ ማስመርመር ይፈልጋል።
ስለሆነም፤ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።
ተወዳዳሪዎች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች:-
1. የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው።
2. የታክስ ማስረጃ፣ የክፍያ ታክስ መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ ያለው፣ እንዲሁም በቅርብ ጊዜ የተሰጠ የታክስ ክሊራንስ (Tax Clearance) ማቅረብ የሚችል።
3. የሙያ ብቃት ማረጋገጫ በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲት ቦርድ (AABE – Accounting and Auditing Board of Ethiopia) የተሰጠ የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያለው።
4. የስራ ልምድ፣
- በፋይናንስ ተቋማት፤ በተለይም በቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበራት ላይ በኦዲት ስራ በቂ ልምድ ያለው።
- በ ‘Peachtree’ ሶፍትዌር የተመዘገበ የሂሳብ መረጃን በማፅዳት ወደ IFRS ስርዓት የመቀየር (IFRS Conversion) እና ይህንኑ ደረጃ ያሟላ የፋይናንስ ሪፖርት የማዘጋጀት በተግባር የተደገፈ ልምድ
የጨረታው ሁኔታ እና መመሪያ
- ተወዳዳሪዎች የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶቻቸውን (Technical and Financial Proposal) በታሸገ ኤንቨሎፕ እና በድርጅቱ ማህተም በማስደገፍ ማቅረብ አለባቸው።
- የማቅረቢያ ቦታ፡- አዲስ አበባ፣ ቦሌ አትላስ፣ አዲስ ሴንቼሪ ሪል እስቴት፣ 8ኛ ፎቅ።
- የምዝገባ ጊዜ:- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ውስጥ።
የማህበሩ መብት:-
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ:-
- ለበለጠ መረጃ: ስልክ ቁጥር 09 09 53 54 79/ 09 52 28 50 09 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
ካፒታል ኃላ/የተ/መሰረታዊ የቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር