የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር በ2019 በጀት አመት ለአገልግሎት የሚውሉ የማገዶ እንጨት፣ የዳቦ አቅርቦት፣ የምግብ ምርቶች እና የእህል ምርት ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር በ2019 በጀት አመት ለአገልግሎት የሚውሉ የማገዶ እንጨት፣ የዳቦ አቅርቦት፣ የምግብ ምርቶች እና የእህል ምርት ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Sep 28, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዥ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር በ2019 በጀት አመት ለአገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት1.የማገዶ እንጨት፣
  • ሎት2. የዳቦ አቅርቦት፣
  • ሎት3. የምግብ ምርቶች እና
  • ሎት4.የእህል ምርት ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ 

የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ።

  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ። የግብር መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው እና የድርጅቱ ህጋዊ
  2. ማህተም ያላቸው።
  3. የጠቅላላ ግዥ መጠን ከብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ማንኛውም የእቃ ግዥ ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ) በላይ እና ለአገልግሎት ከ10,000.00 (አስር ሺ ) ብር በላይ ሶስት በመቶ ቅድመ ግብር የሚቀነስ ይሆናል።
  5. የእቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥውን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ የውልማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ አስር (10) በመቶ በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ፣የታደሰ ንግድ ፈቃድ ፣ ቲን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል እና ሰነድ የተገዛበት ደረሰኝ ኮፒ በአንድ በታሸገ ፖስታ እና በሌላ ፖስታ ኮፒ በማድረግ በፖስታው ላይ ኮፒና ኦርጅናል ብለው በመጻፍ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ ተደርጎ በት/ቤቱ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
  8.  ለጨረታ ሰነድ ለመግዛት ብር 200 (ሁለት መቶ ) ከት/ቤቱ ገንዘብ ያዥ ገቢ በማድግ ሰነድ መግዛት አለባቸው።
  9. ጨረታው ከመስከረም 18/2019 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት በጋዜጣ ታትሞ ይቆያል።
  10.  ጨረታው በ11ኛው ቀን መስከረም 28/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል። ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል።
  11. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ወይም ኮሬክሽ ካለው ፍሉድ መጠቀም አይፈቀድም።
  12. ት/ቤቱ በሚቀርቡ እቃዎች ላይ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።
  13. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን፤ እቃዉን በራሱ የትራንስፖርት ወጭ እና የጫኝ አውራጅን ወጭ ታሳቢ በማድረግ የሚወዳደር ሲሆን በወቅቱ ሀዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ማቅረብ አለበት።
  14. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 144/2018 መሰረት ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፡
  16. አድራሻ ደ/ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግቢ ስልክ 09 20 50 43 80/ 09 20 50 68 87/ 09 37 37 28 10 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡።

ሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *