Addis Zemen (Sep 30, 2026)
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ01/2019ዓ.ም
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የዓድዋ በር የመ/ደ/ት/ቤት 2019 ዓ.ም ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ሎት |
የጨረታው አይነት |
|
የጨረታው ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን |
|
1 |
ሎት 001 |
የደንብ ልብስ እና የስፖርት መምህራን ትጥቅ |
ናሙና የሚቀርብበት |
8307.61 |
|
2 |
ሎት 002 |
አላቂ የቢሮ እና የትምህርት ዕቃዎች (የፅሕፈት መሣሪያዎች) |
ናሙና የሚቀርብበት |
8000.00 |
|
3 |
ሎት 003 |
የጥገና ዕቃዎች (የሕንፃ መሣሪያዎች) |
ናሙና የሚቀርብበት |
6000.00 |
|
4 |
ሎት 004 |
የማሽነሪ ጥገና ሥራ (ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ) |
የሥራውን ሰነድ በመግዛት |
1000.00 |
|
5 |
ሎት 005 |
የንፅሕና መጠበቂያ ዕቃዎች የፅዳት እቃዎች |
ናሙና የሚቀርብበት |
8383.20 |
|
6 |
ሎት 006 |
የቢሮ ማሽነሪ (ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ወንበር፣ ጠረጴዛ ወዘተ ቋሚ ዕቃዎች |
በፎቶ ናሙና የሚቀርብበት |
7500,00 |
|
7 |
ሎት 007 |
የት/ቤቱ ለሚሰጠው ስልጠና የውሃ፣ ቆሎ፣ ኩኪስ እና የመሳሰሉትን አቅርቦት ለዓመት በውል ማቅረብ |
ሰነድ በመወሰድ |
5000.00 |
|
8 |
ሎት 008 |
የህትመት ሥራ |
መጥተው ሥራውን በማየት |
1000.00 |
|
9 |
ሎት 009 |
የሕከምና እቃ |
በናሙና የሚቀርብበት |
200.00 |
|
10 |
ሎት 010 |
የላብራቶሪ እቃዎች |
በናሙና የሚቀርብበት |
8000.00 |
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በፌዴራል የመንግሥት ግዥ አስተዳደር የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመዘገብ የምስክር ወረቀት፣ የቫት ሰርተፍኬት፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር /200/ ሁለት መቶ ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ት/ቤቱ ፋይናንስ የሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላል።
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበት አይነት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በዓድዋ በር የመ/ደ/ትቤት ስም በየሎቱ በተዘረዘረውና በተቀመጠው የገንዘብ መጠን መሠረት ነው።
4. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት የሚጫረቱበት ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኦርጅናል እና ኮፒውን ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
6. አሸናፊ ድርጅት ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ እቃ ናሙና ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን ናሙና ያልቀረበበት እቃ ከውድድር ውጪ የሚሆን ስለሚሆን በርከክብ ቀን ባቀረበው ናሙና መሰረት ገቢ የሚደረግ ሲሆን ካላቀረበ ያስያዘው CPO ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
7. በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መጠን በላይም ሆነ በታች በተመደበለት በጀት ጋር አጣጥሞ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀን ተዘግቶ በቀጣዩ የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ውስጥ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ላይ በግልፅ ይከፈታል።
9. ጨረታው ተከፍቶ አሽናፊው ድርጅት ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ውል በሚዋዋልበት ጊዜ ባሸነፈበት ዕቃዎች መጠን 10% CPO ወይም የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
10. ለማሽነሪ ጥገና የምትወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ት/ቤቱ ለ1ዓመት በውል እንደምትሠሩለት ውል በመግባት ይሆናል ስለዚህ ለጥገና በምትወዳደሩበት ጊዜ የምትሰጡት ዋጋ ዓመታዊ ዋጋ መሆን ይጠበቅበታል የጥገና ሥራው ተቀያሪ ዕቃን አያካትትም።
11. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ (ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
12. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. ተጫራች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም መምታት ይኖርበታል።
አድራሻ፡- የካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ጽ/ቤት ጀርባ የቀድሞ 09 መብራት ኃይል አጠገብ
ለበለጠ መረጃ፡- 011 636-6555
በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የዓድዋ በር የመ/ደ/ት/ቤት