በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ ለመስሪያ ቤቱ ለአገልግሎት የሚውሉ አገልግሎቶችን እና እቃዎችን መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ ለመስሪያ ቤቱ ለአገልግሎት የሚውሉ አገልግሎቶችን እና እቃዎችን መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 02, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ ለመስሪያ ቤቱ ለአገልግሎት የሚውሉ አገልግሎቶችን እና እቃዎችን በጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።

የእቃ ዝርዝር

የCPO መጠን በብር

ሎት 1 የአላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ

5,000

ሎት 2 የፅዳት እቃዎች ግዥ

5,000

ሎት 3 የደንብ ልብስ ግዥ

10,000

ሎት 4 የቋሚ የቢሮ እቃዎች ግዥ

10,000

ሎት 5 የህትመት ግዥ

5,000

ሎት 6 የመድሀኒቶች ግዥ

10,000

ሎት 7 የጥገና እቃዎች ግዥ

5,000

ሎት 8 የኤሌክትሮኒክስ ማሽነሪዎችና እቃዎች ጥገና

10,000

ሎት 9 የሽንት ቤትና የህጻናት ማቆያ ቦታዎች እድሳትና ጥገና

5,000

ሎት 10 የላብራቶሪ ሬኤጀንቶች ማቅረብና የባዮ ሜዲካል ጥገና

20,000

በባንክ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በደብዳቤ የምትወዳደሩ ተጫራቾች በፅህፈት ቤቱ የበላይ ሀላፊ የተፈረመ ህጋዊ ደብዳቤ በማስያዝ መግዛት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን፡፡ስለዚህ የተጠየቁትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች ለአንድ ሎት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) እና በተጨማሪ ቋሚ የህክምና እቃ ጨረታ ላይ የሚትወዳደሩ ተጫራቾች ከጤና ጽ/ቤት የተሰጠውን ስፔስፊኬሽን መውሰድ ያለባችሁ መሆኑን እያሳወቅን፤ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነድ ገዝታችሁ መወዳደር የሚትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

ተጫራቾች ጨረታ ለመካፈል ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች:-

1. ህጋዊ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት።

2. የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ በየ ዘርፉ ያላቸው መሆን አለበት።

3. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።

4. ቫት የተመዘገቡበትን ሰርተፈኬት ማቅረብ የሚችል መሆን አለባቸው።

5 . በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚረጋገጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው።

6. የግብር ከፋይነት ቲን ሰርተፍኬት መቅረብ አለበት።

7. ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ገቢ ማድረግ አለባቸው።

8. ናሙና ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ይሆናሉ፡፡ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናልን እና ፎቶ ኮፒ በመለየት የሚወዳደርበትን የሎት አይነት በፖስታ ላይ መገለፅ አለበት፡፡ በተጨማሪ ቋሚ የህክምና ዕቃዎችን የምትወዳደሩ ተጫራቾች የፋይናንሻልና የቴክኒክ መግለጫዎችን በተለያዩ ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡ የሚወዳደርበትን ሎት በግልፅ በፖስታው ጀርባ ላይ ያልገለፀ ተጫራች አይስተናግድም(ውድቅ ይደረጋል)፡፡ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 46 በኮሚቴዎች ይከፈታል።

  • ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት።
  • እያንዳንዱ ሰነድ ላይ የተጫራቾች ፊርማና የድርጅታችሁ ማህተም መኖር አለበት።
  • መ/ቤታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ የጨረታውን ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካጋጠመ ተጫራቹ ስርዙ ጎኑ ላይ ፊርማውን ማስቀመጥ ይኖርበታል።
    አድራሻ፡- ወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ገደራ ሳራ አምፖል አካባቢ

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የ ወረዳ 14 ህዳሴ ጤና ጣቢያ