ሳምራዊት ፋውንዴሽን የህጻናት፣ የአረጋውያንና የአካል ጉዳተኞች መርጃ ድርጅት ለድርጅቱ ከ2025 እስከ 2027 የሂሳብ ዓመት የውጭ ኦዲት ሥራ ለማስፈጸም ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ሳምራዊት ፋውንዴሽን የህጻናት፣ የአረጋውያንና የአካል ጉዳተኞች መርጃ ድርጅት ለድርጅቱ ከ2025 እስከ 2027 የሂሳብ ዓመት የውጭ ኦዲት ሥራ ለማስፈጸም ይፈልጋል


Reporter (Oct 04, 2026)

ሳምራዊት ፋውንዴሽን

SAMRAWIT FOUNDATION

የውጭ ኦዲት አገልግሎት ጥሪ (CALL FOR AUDIT SERV]CES)

ድርጅታችን ሳምራዊት ፋውንዴሽን የህጻናት፣ የአረጋውያንና የአካል ጉዳተኞች መርጃ ድርጅት ለድርጅቱ ከ2025 እስከ 2027 የሂሳብ ዓመት የውጭ ኦዲት ሥራ ለማስፈጸም ብቃትና ልምድ ያለው የኦዲት ድርጅት እንዲያመለክት ጥሪ ያቀርባል።

1. የሥራው ዓላማ

የኦዲት አገልግሎቱ የድርጅቱን የፋይናንስ መዝገቦች፣ የገቢና ወጪ ሂሳቦች፣ የንብረትና የዕዳ መዝገቦች እንዲሁም የዓመቱ የፋይናንስ ሪፖርቶች ተገቢውን የሂሳብና የኦዲት መስፈርት በመከተል በግልጽነትና በነፃነት መመርመርን ያካትታል።

2. አመልካቾች ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች

አመልካቾች ከሚከተሉት ሰነዶች ጋር ማመልከት አለባቸው፦

  1. በAABE የተሰጠ እና የታደሰ የኦዲት ሙያ ፈቃድ ሊኖረው ይገባል
  2. በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ሕጋዊ የኦዲት አገልግሎት ለመስጠት የተፈቀደለት መሆን አለበት፤
  3. የኢትዮጵያን የሂሳብ፣ የታክስና የCSO ሕጎችና መመሪያዎች የሚያውቅ መሆን ይጠበቅበታል፤በተመሳሳይ ድርጅቶች የኦዲት ሥራዎችን በተሳካ ሁኔታ የሠራበትን ማጣቀሻ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል።
  4. የኦዲት ፈቃድ ቅጂ፤
  5.  የንግድ ፈቃድ ቅጂ፤
  6. TIN ሰርተፊኬት ቅጂ፤
  7.  የታክስ ክሊራንስ/የግብር ክፍያ ማረጋገጫ፣
  8. የድርጅቱ/ኦዲተሩ የሥራ ልምድ መግለጫ፤
  9. በNGO/CSO የተሠሩ ተመሳሳይ የኦዲት ሥራዎች ዝርዝር፤
  10. የቀድሞ ደንበኞች ማጣቀሻ፤
  11. የቴክኒክና የፋይናንስ ፕሮፖዛል፤

የማመልከቻ ማስገቢያ

ፍላጎት ያላቸው እና መስፈርቱን የሚያሟሉ የኦዲት ድርጅቶች/ባለሙያዎች የቴክኒክና የፋይናንስ ፕሮፖዛላቸውን ከላይ ከተጠቀሱት ሰነዶች ጋር በመያያዝ እንዲያቀርቡ ይጋበዛሉ።

 የመጨረሻ የማመልከቻ ቀን፦ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣ በ10 ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው::

አድራሻ፡– ቦሌ ቡልቡላ ቅዱስ ገብርኤል ህንጻ ስምንተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 በአካል በመቅረብ ማመልከት ይቻላል:: ወይም በEmail, samrawitfoundationgmail.com  መላክ ይችላሉ::

በተጨማሪም በስልክ ቁጥር 0985850858 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል::


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *