Addis Zemen (Oct 03, 2026)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የግልጽ ጨረታ መመርያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወርዳ 11 አስተዳደር ስር የሚገኝ የሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት አመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
- ሎት 01 የመምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች የደንብ ልብስ የአስፖርት ትጥቅ፣
- ሎት 02 የትምህርት እቃዎች፣
- ሎት 03 የህትመት ስራዎች፣
- ሎት 04 የህክምና እቃዎች፣
- ሎት 05 የፅዳት ሌሎች አላቂ እቃዎች እና አቅርቦቶች
- 06 ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሣሪያ እድሳት እና ጥገና
- 07 ለህንጻ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እደሳት እና ጥገና
- ሎት 08 ለህንፃ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚ መግዣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ማሰራት ይፈልጋሉ።
እያንዳንዱ ተጫራች የሚከተሉትን ነጥቦች በመረዳት የጨረታ ሰነዳቸውን በዚህ መመሪያ መሰረት አሟልተው እንዲያቀርቡ ያስፈልጋል።
1. ተጫራቾች የዘመኑ ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስቴር ወይም በአዲስ አበባ ከተማ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገቡትን የምስክር ወረቀትና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም በኤጀንሲው ድረ-ገጽ/ዌብሳይት/ www.ppa.gov.et መገኘት አለባቸው።
2. የጨረታ ሰነዱ በፖስታ ታሽጎ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሳጥን የሚታሸግበት ሰዓት ከመድረሱ በፊት መግባት ይኖርበታል።
3. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1_8 ከተዘረዘሩት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ በተጨማሪ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር የስራ ሰዓት እስከ 11፡30 የጨረታ ሰነድ በሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ክፍያ ሂሳብ አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት በመቅረብ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ከፍሎ በመውሰድ ከቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዓይነት ውስጥ የተዘረዘሩትን እቃዎች ያአንዱን እቃ ዋጋ ቫትን ጨምሮ በግልጽ ማስፈር አለባቸው
5. ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን አድራሻቸውንና ፊርማቸውን በእያንዳንዱ የሰነድ ገጽ ላይ በማኖር በማህተም ማረጋገጥ አለባቸው።
6. በጨረታ አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ድርጅት ከመስሪያ ቤቱ የበላይ ኀላፊ ጋር በሚገባው ውል መሰረት እቃዎቹን እንዲያስገባ ሲታዘዝ በራሱ ወጪ እቃ ግምጃ ቤታችን ድረስ አቅርቦ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት።
7. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያነት የሚያገለግል የገንዘብ መጠን በየጨረታ ሎት ተከፋፍሎ እንደሚከተለው ቀርቧል።
- ሎት 01 የመምህራንእና የአስተዳደር ሰራተኞች የደንብ ልብስ በዚህ ከፍል የተጠየቀው የብር መጠን 7,500.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
- ሎት 02 የትምህርት እቃዎች 7,590.00 ብር በ0.5% ተሰልቶ
- ሎት 03 የህትመት ስራዎች 2,500.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
- ሎት 04 የህክምና እቃዎች 450.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
- ሎት 05 የፅዳት /ሌሎች አላቂ እቃዎች እና አቅርቦቶች 3,250.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
- ሎት 06 ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳት እና ጥገና 3,750.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
- ሎት 07 ለህንጻ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እደሳት እና ጥገና 4,000.00 ብር በ 0.5% ተሰልቶ
- ሎት 08 ለህንፃ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚ 10,500.00ብር በ 0.5% ተሰልቶ መሆኑን አውቃቹ ተጫራቾች ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቬሎፕ አሽጎ በጨረታ ሳጥን ውስጥ በመስሪያ ቤታችን ስም ማሲያዝ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የጨረታ ሰነዱን የሚሞላ ክፍል በአግባቡ ሞልቶ ተመላሽ ያላደረገ አቅራቢ ከጨረታ እንደሚሰረዝ አናሳስባለን።
8. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች በዚህ ጨረታ እንዲወዳደሩ እየተጋበዙ እንዲሁም ካደራጃቸው አካል ለጨረታ ሰነድ ግዥ በጨረታ ማስከበሪያነት የሚያገለግል በመስሪያ ቤቱ ስምና ሀላፊነት መውሰድ በሚችል አካል የተፃፈ ደብዳቤ እና አምራች መሆናቸው የሚገልፅ ማስረጃ ማቀረብ ይኖርባቸዋል። ይህንን ማቅረብ ካልቻሉ እነደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይገዛሉ የጨረታና የውል ማስከበሪያ ያሲዛሉ።
9. የጨረታ ሳጥኑ ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
10. ጨረታው ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በሚቀጥለው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ላይ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የባዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል። ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ እቃ ከጨረታው መዝጊያ ሰአት ከሁለት ቀን በፊት ናሙናዎችን ማቅረብና ለግዥ (ለተወከለው) ሰራተኛ ማስረከብ ይኖርበታል። ናሙና ማቀረብ የማይቻልባቸው ቋሚ እቃዎችን በፎቶ በማስደገፍና ስለ እቃው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ማቅረብ አለባቸው።
11. የመ/ቤቱ የእቃ ጥራት ተቆጣጣሪ ኮሚቴ(የቴክኒክ ኮሚቴ)ያቀረቡትን የእቃዎቹን ጥራት አይቶ ከመስሪያ ቤቱ ፍላጎት ጋር የማይጣጣም ነው ብሎ ካመነ ዕቃው እንዲመለስ ማድረግ ይችላል።
12. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት/ድርጅቶች ማሸነፉ እንደተገለፀለት በተሰጠው የጊዜ ገደብ ከ7ኛው – 15ኛው ቀን ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ በጨረታ ማስከበሪያነት ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ሆኖ መ/ቤቱ እንደ ምርጫው ሁለተኛው ወይም ሶስተኛው የወጣውን ተወዳዳ ሊጋብዝ ይችላል።
13. የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ ለውል ማስከበሪያነት የሚውል ያሸነፉትን እቃ ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
14. የግዥ ውል በሚፈፀምበት ጊዜ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነድ ላይ የተመለከተውን የእቃ ብዛትና ተያያዥ አገልግሎቶች እሰከ 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይቸላል።
15. ለቋሚ እቃዎች እና የማሽን ቀለሞች ትክክለኛ ለመሆናቸው አሸናፊ ተጫራቾች ለአንድ አመት ዋስትና ይሰጣል።
16. መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው በድርጅቱ የስራ ቦታ በመገኘት የእቃዎችን ጥራትና የድርጅቱን አቅም ለመገምገም ቢፈልግ ድርጅቱ የመተባበር ግዴታ አለበት።
17. ለውድድር የሚቀርበው የጨረታ ሰነድ ኮፒ ከኦርጅናል ሰነድ ጋር ለየብቻ ማቅርብ ይኖርበታል። በተጨማሪም ተጫራቹ የገዛው ሙሉ ስነድ ኮፒ እና ኦርጅናል ሙሉ በሙሉ ተመላሽ ካላደረገ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
18. በመ/ቤታችን ለእቃ ጥራት ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ በመሆኑ ተወዳዳሪዎች የተሻለ ጥራት ያላቸውን እቃዎች እንዲያቀርቡ ይበረታታሉ።
19. ለማጭበርበር የሞከረ ተጫራች ከጨረታው ይሰረዛል።
20. የእቃውን ዋጋ ማቅረብ የምትችሉት ት/ቤቱ በሸጠላቹ ሰነድ ብቻ ሞልታቹ ማቅረብ አለባችሁ።
21. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ከአጠና ተራ ሎሚ ሜዳ ሲደርሱ ወደ ግራ 200 ሜትር ገባ ብሎ ኢንደስትሪ መንደር አካባቢ የሚገኘው የሶርአምባ የመ/ደ/ት/ቤት
አዲስ አበባ አዲስ ከተማ
ስልክ ቁጥር 011-827-7801
የሶር አምባ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት