Reporter (Oct 04, 2026)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. (በቀድሞ ስሙ ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ) ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣንና ውክልና መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪው ቅርንጫፍ |
የመያዥ ንብረቱ መለያ |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ |
ሐራጁ የሚከናወንበት |
||||||
|
የተሽከርካሪው አይነት |
የሰሌዳ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
የሻሲ ቁጥር |
ሞዴል |
ቀን |
ሰዓት |
|||||
|
አቶ ምሩፅ ገዛኢ አድሃና |
ተበዳሪው |
ቦሌ ሚካኤል |
ሃዩንዳይ |
አአ-02-B61029 |
G4F JKZ902449 |
TMAJ3812HLJ929286 |
2019 |
3,700,000.00 |
ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም |
4:00-5:30 |
|
የጨረታ ደንቦች፡–
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ስም የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) በማስያዝ መመዝገብ ይችላሉ።
- የተጫራቾች ምዝገባ ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል። በጨረታው የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም።
- ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለጸው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ላይ ይካሄዳል።
- በጨረታው ላይ ተጫራቾች፣ አስያዥና ተበዳሪ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው መገኘት ይችላሉ። ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል፡፡
- የንግድ ማህበራትን ወክሎ ለመጫረት የማህበሩን መመስረቻ ፅሁፍ የያዘና በማሀበሩ ስም ንብረት ለመግዛት ስልጣን ያለው መሆን ያለበት ሲሆን ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ በማቅረብ ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ የተገለጸለት ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል። ባይከፍል ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል። ላላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
- በንብረት ማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈል ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የሊዝ ክፍያ ወይም ሌላ ማንኛውንም ክፍያ ገዢው ይከፍላል።
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።
- ለበለጠ ማብራሪያ ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዋናው መሥሪያ ቤት በስልክ ቁጥር 011 5 31 81 17 (የህግ አገልግሎት መምሪያ) ወይም 0116 39 27 76 (ቦሌ ሚካኤል ቅርንጫፍ) ደውሎ መጠየቅ ወይም የህግ አገልግሎት መምሪያ በአካል ቀርቦ ማነጋገርና ንብረቱን የሚጎበኙበት ሁኔታ ማመቻቸት ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።