በአዊ ብሔረሰብ አስተዳር የዚገም ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመቱ ለወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳር የዚገም ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመቱ ለወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል


Be'kur (Oct 12, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳር የዚገም ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመቱ ለወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ

  • 1ኛ. የጽህፈት መሳሪያ፣
  • 2ኛ. ኤሌክትሮኒከስ እቃዎች፣
  • 3ኛ. የተዘጋጁ የደንብ ልብሶች፣
  • 4ኛ. ብትን ጨርቅ፣
  • 5ኛ የስፖርት ትጥቅ፣
  • 6ኛ. የተዘጋጁ ጫማዎች፣
  • 7ኛ.የመኪና ጎማ፣
  • 8ኛ.የፅዳት ዕቃዎች፣
  • 9ኛ. የስፖርት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ጋር ውል በመያዝ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ወይም በዘርፉ የተሰማሩ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የሚገዛው የግዥ መጠን ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባችኋል፤ ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና ማስረጃዎችን ማለትም የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ቲን ሰርተፊኬትና ቫት ሰርተፊኬት የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ፖስታ ውስጥ በማስገባት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 11፡30 ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ዚገም ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ ቤት ፋይናንስ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 4 የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ
  5.  የማወዳደሪያ ሥርዓቱ በየሎቱ በጥቅል ድምር ነው፡፡
  6. የሁሉም የእቃ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዟል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች ለጽህፈት መሳሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 20‚000 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ለተዘጋጁ የደንብ ልብሶች 15‚000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)፣ ለብትን ጨርቅ 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ፣ለስፖርት ትጥቅ 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)፣ ለተዘጋጁ ጫማዎች 12,000 (አስራ ሁለት ሺህ ብር)፣ ለስፖርት እቃዎች 10,000 (አስር ሽህ)፣ ለፅዳት ዕቃዎች 3,000 (ሶስት ሽህ ብር)፣ ለመኪና ጎማ 15,000 (አስራ አምስት ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ለስድስት ወር የሚቆይ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በወረዳው የገቢ ደረሰኝ መሂ-1 ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው ከተገለጸው ውጭ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ ዚገም ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሠዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የጨረታ ሳጥኑ ከሚታሸግበት የመጨረሻ ሰዓት እና ደቂቃ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚገም/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በ11ኛው ቀን የጨረታ ሣጥኑ ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጐ ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ካልተገኙ የጨረታ ሰነዱ እንዲከፈት ተደርጎ ያልተገኙ ተጫራቾች ግን በእለቱ ለሚተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  10. ተጫራቾች ንግድ ፈቃዳቸው በሚጋብዛቸው ብቻ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ይሁን እንጅ የሚሞላዉ ዋጋ ማንኛዉንም የመንግስት ግብር፣ የትራንስፖርት ወጭና ሌሎች ውጭዎች ካሉ ማካተት ይኖርበታል፡፡
  11. ተጫራቾች የአሸነፉትን እቃ ዚገም ወረዳ ገ/ኢ/ል ጽ/ቤት ድረስ በራሳቸው ወጭ በማምጣትና በባለሙያ እና በጥራት አረጋጋጭ ኮሚቴዎች በማስፈተሽ ወይም በማስመርመር የማስረከብ ግዴታ አለባቸዉ፡፡
  12. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነው፡፡
  13. መ/ቤቱ ሃያ በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. የደንብ ልብስ ተጫራቾች የሚሞሉትን ደንብ ልብስ ሳምፕል ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሚቀርበው ደንብ ልብስም በናሙናው መሠረትና በደንብ ልብስ አጠቃቀም መመሪያ ሁኖ ናሙናው ተቀባይነት ያለገኘ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ስልክ ቁጥር 058 556 87 60 /09 13 71 74 22 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡

የዚገም ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት