በድሬዳዋ አስተዳደር የድልጮራ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ ለ2 (ሁለት ዓመት) የሚውል የጥበቃ አገልግሎት በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ህጋዊና ብቁ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በድሬዳዋ አስተዳደር የድልጮራ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ ለ2 (ሁለት ዓመት) የሚውል የጥበቃ አገልግሎት በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ህጋዊና ብቁ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen (Oct 12, 2026)

በድጋሚ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ድ/ ዴ /ድ/ጮ/ሆ/03/19

በድሬዳዋ አስተዳደር የድልጮራ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ ለ 2 (ሁለት ዓመት) የሚውል የጥበቃ አገልግሎት በግልፅ በጨረታ አወዳድሮ አገልግሎቱን ለመግዛት ህጋዊና ብቁ ተወዳዳሪዎችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች

  1. ተጫራቾች በዘርፉሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ለ2019 ዓ.ም ግብር የከፈሉ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል።
  3. በመንግስት ግዢ አቅራቢ የተመዘገቡና የተመዘገቡበትን ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ከፌዴራል ፖሊስ የታደሠ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  4. ተጫራቾች የታክስ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺ ብር) በመክፈል በድል ጮራ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር A/02 በመቅረብ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
  6. መስፈርቱን የሚያሟላ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ወይም (CPO) ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የጨረታሠነዱን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ ተብሉ በተዘጋጀው የጨረታ መቀበያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታ ሰነዱ የሚከፈትበት ቀን ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራ ቀናት ከቆየ በኋላ በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ ከቀኑ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግዢ ፋ/ን/አስ ዳይሮክትሬ ቢሮ ቁጥር A/02 ይከፈታል።
  9. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ እንደተገለፀለት አስፈላጊውን የጨረታ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከሆስፒታሉ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ይህ ባይፈፀም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስትገቢ ይሆናል።
  10. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፤ ሙሉ አድራሻቸውን እና ፊርማቸውን እንዲሁም የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  11. ከግል ስራና አገናኝ ኤጀንስ በአገር ውስጥ ስራና ሠራተኛ የማገናኘት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
  12.  ሆስፒታሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

 ኣድራሻ:- በድሬዳዋ አስተዳደር የድል ጮራ ሆስፒታል
ስልክ ቁጥር:- 025-211-5692/0982 540 408/0901 10 3211፤ ፖስታ ሳጥን ቁጥር 177
በድሬዳዋ አስተዳደር የድልጮራ ሆስፒታል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *