በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Lessan (Oct 17, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ስፖርት ምክር ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

1. የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ ግዢ

ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች አግባብነት ያለው በዘመኑ የታደሰ የንግድ ምዝገባ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው።
  2. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ ማስረጃ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ ለመሆናቸው የተጫራቾችን የምስክር ወረቀትና የግብር ከፋይነት መለያ ሰርተፊኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና ስርተፊኬት ማቅረብ
    የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የዕቃውን ስፔስፊኬሽን ዝርዝር መግለጫ/ ከሚያቀርቡት ዋጋ ጋር አያይዘው ስፖርት ጽ/ቤት ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ዋጋ ብር 10,000 /አስር ሺ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቦሌ ክፍለ ከተማ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ዲዛይንና ግንባታ ፑል ፋይናንስ አስተዳደር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 215 በመምጣት ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ የኢትዮዽያ ብር 300 ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለየብቻ አንድ ዋና እና አንድ ቅጅ በማድረግ በሰም በታሸጉ በተለያዩ ኢንቨሎፖች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዋናውን ዋና/orginal/ እና ቅጅውን ቅጅ /copy/ በማለት በግልጽ በሚታይ ጽሑፍ በፖስታዎቹ ላይ በመጻፍ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ከላይ በተጠቀሰው ቀን በቦሌ ክ/ከተማ ስፖርት ጽ/ቤት በመቅረብ በጽ/ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የመጀመሪያ የሥራ ቀን የሚገባ መሆኑን እንገልጻለን።
  7. ጨረታውን በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በመሆኑም ጨረታው ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በክ/ከተማው 7ኛ ፎቅ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ግን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የመጀመሪያው የስራ ቀን የሚገባ መሆኑን እንገልጻለን።
  8. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝና ከስፖርት ም/ቤቱ የግዥ ውል ስምምነት መፈጸም ይኖርባቸዋል።
  9. ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርት ሳያሟሉ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ መሞከር ከጨረታው ያሰርዛል።
  10. የጨረታው ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ ም/ቤቱ ጠቅላላ ለጨረታው ከቀረበው የእቃ ብዛት 20% ከፍና ዝቅ ብሎ የግዥ ትዕዛዝ ሊሰጥ ይችላል።
  11. ለጨረታው የተሰጠው ዋጋ ለ60 ቀናት ጸንቶ ይቆያል።
  12. ም/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ተጫራቾች ይፋ በሚደረገው ውጤት ቅሬታ ካላቸው በ5 ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን የማቅረብ መብት አላቸው።
  14. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማስረከብ ግዴታ አለባቸው።
  15. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ ባቀረቡት ሳምፕል (ናሙና) መሰረት አይነትና ብዛት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በአድራሻችን በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 13 61 60 49/ 09 10 09 70 71 ደውለው ያነጋግሩን።

ማሳሰቢያ፡- ሲፒኦ ሲዘጋጅ ቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ስፖርት ም/ቤት Bole sub city administration sport council በሚል ይዘጋጅ

አድራሻ፡- መገናኛ አደባባይ አጠገብ ቦሌ ክ/ከተማ አስተዳደር 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 707 ስፖርት ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቦሌ ክ/ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *